ፍቅረኛዬን በሌላ ስልክ ቁጥር ሌላ ሴት ሆኜ እያዋራሁት እኔ ፍቅረኛው እያለሁ ሌላ ሴት ለማውራት ያለው ጥድፊያ የሚልከው ሜሴጅ ስለ እኔ ያወራል ብዬ ብጠብቀው ፍቅረኛ እንደሌለው ሆኖ አዋራኝ የሌላ ሴት ፎቶ ብልክለት ቆንጆ ነሽ እያለ አሽኮረመመኝ መጨረሻ ላይ በራሱ እኔ እንደማዋራው ጠርጥሮ ነው መሰለኝ በዋናው አካውንቴ አንች ነሽ አይደል በዚህ ቁጥር የምታዋሪኝ አለኝ እና ልቤን እንደሰበረውና እንደሌሎቹ ወንዶች ልክስክስ እንደሆነ ነገርኩት እሱ ግን አንች መሆንሽን ጠርጥሬ ስለነበር እንድታወሪኝ ያደረኩት ፎቶ የላኩልሽ ማንነትሽን በደንብ ለማወቅ ነው ስላውራሁሽም አንች መሆንሽን አውቂያለሁ ምንም ያጠፋሁት ነገር የለም አንችስ ካፈቀርሽኝ እንዴት ተጠራጥረሽ ትፈትኝኛለሽ ብሎ ተቆጣ አሁን ተኮራርፈናል ቢያወራኝ እፈልጋለሁ እሱ ግን ተናዷል እኔም እሱን ለማውራት አስጠላኝ ምክንያቱም ልቤን ሰብሮታል እኔ ግን ምንም ሊዋጥልኝ አልቻለም በዚህ አይነት ሌሎች ሴቶችንም እንደሚያወራቸው ነው የተረዳሁት ግን አፈቅረዋለሁ ላጣው አልፈልግም ነበር ቆይ እንዴት ብዬ ልመነው በዛ ላይ ሳወራው የነበረው በእህቴ ስልክ ስለነበረ አለመታመኑን ሁሉም እህቶቼም አወቁ ታማኝ ነው ብዬ ያፈቀርኩት ፍቅረኛዬን በእህቶቼ መካከል አሳፈረኝ
Aug 05, 2024አይ ፍቅር🙃 በቃ manipulate ሲያረግሽ ታምኝዋለሽ he is playing ግልፅ ነው ፊትሽ ሌላ ሴት እስኪገለጭጭ ነው ምጠብቂው?😒
Aug 05, 2024