This question is for my 96's babies( በኢትዮጵያ አቆጣጠር). ብዙ መወያየት ያለብን ነገር ስላለ ገባ ገባ በሉ:: ቆይ እኛ ምንድነው የምንባለው አድገናል እያደግን ነው ወይስ ልናድግ ነው? ሴቶች ካላቹ ስለማይመለከታቹ አሳልፉት በእናንተ ጣጣ ነው እዚህ ሀሳብ ውስጥ የገባሁት😒:: ቆይ የት ለመድረስ ነው ጥድፊያው? አብዛኛው እኔ የማውቃቸው እኩዮቼ ሴቶች አግብተዋል ብቻ ሳይሆን ወልደዋል😳:: እናም ይሄን ውይይት ለወንዶች ተውልን:: አደራ እዚህ እየገባቹ እናት ሆኛለው አያት ሆኛለው እንዳትሉን🤐:: እናም ወደ ጥያቄዬ ስመለስ እኩዮቼ ወንዶች ምን ደረጃ ላይ ናችሁ? ከትምህርት ውጪ ባለው ህይወታቹ ማለቴ ነው:: ሌላው ደግሞ ከ20ዎቹ የወጣቹ ሰዎች ካላቹ ለአዲስ ገቢዎች ምን ትመክሩናላቹ:: የሚቆጫቹ ነገር ካለና ወደኃላ ለመመለስ እድል ቢሰጣቹ ልታደርጉት የምትችሉት ነገር ካለ ንገሩን:: Thank you 😊
Aug 04, 2024Hey kid አትጨናነቅ ሁሉም በጊዜው ይሆናል ብቻ ሱስ ውስጥ አትግባ
Aug 04, 2024