#education
ሰላም ቤተሰቦች 🤗🤗🤗 12ን 2014 ነበር የተፈተንኩት እና ውጤት አልመጣልኝም ከዛን ኮሌጅ ገብቼ የመማር ፍላጎት ቢኖረኝም ቤት ውስጥ በነበረው ምክንያት የተነሳ እስካሁን ከትምህርት አለም እርቂያለው የእናቴ አለመኖር ቤት ውስጥ ያለው ሀላፊነት እኔ ላይ ወድቋል አባቴ ፊልድ ነው የሚሰራው በሳምንትም በሁለት ሳምንትም አንዴ እየመጣ አንድ ቀን አድሮ ይመለሳል ሁለት ታናሽ ወንድሞችም አሉኝ እነሱ የኔ ሀላፊነት ናቸው የመኪና እረዳትነትም ሰራለው እና አሁን መማር ፈለኩ ቢያንስ የርቀት እንኳን መማር እንዳለብኝ ይሰማኛል እና ምን መማር እንዴት መማር እንዳለብኝ ግራ ገብቶኛል 12ን ተፈትኜ እንደጨረስኩ ራቅ ወዳለ ሰፈርም ስለቀየርን ሁሉ ነገር ግራ ስለገባኝ ነው ምን እንድማር ትመክሩኛላቹ ስለትብብራች አስቀድሜ ማመስገን ፈልጋለው🙏🙏🙏
Aug 01, 20242 engagements