ጥያቄዬ ለኦርቶዶክስ ወንድም እህቶቼ ነው በፆመ ፍልሰታ ሱባኤ መያዝ ፈልጌ ነበር እና 1.ፔሬዴ ከ1 ሳምንት በላይ እንድይዝ የሚያደርገኝ አይመስለኝም ቀኑን ስቆጥረው ማለት ነው 2.ሱባኤ የምትይዙትን ምክንያት እወቁ የሚል ነገር አለ እና እኔ ቢያንስ ሰለ ሀጥያት በደል ምህረት ለመለመን ነው በዚህስ ጉዳይ ምን ትላላችሁ የምታውቁትን በማካፈል ተባበሩኝ አመሰግናለሁ🙏
Aug 01, 2024ሱባኤ ማቋረጥ ትልቅ ሰህተት ነው እንደምታቋራጪ እያወቅሽ ደሞ ባትገቢ ይሻላል። ሱባኤ የምትይዙበት ምክንያት ማወቅ ሚያስፈልገው ሰቡኤ ሲባል ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት ማለት ነው ማለትም ከአለም ተለይቶ ለነብስሽ ብቻ ምትኖሪበት ጊዜ ነው ስለዚ እግዚአብሔርን እንዲያረግልሽ ምትፈልጊውን ነገር ቀድመሽ አውቀሽ ትገብያለሽ ማለት ነው እንደዚ ሲባል ግን ስጋዊ ፍላጎት ሳይሆን እንዳልሽው ኃጥያትሽን እያሰብሽ ምህረት እንዲያረግልሽ እናም ለመንፈሳዊ ነገርሽ ምትጠይቂበት ነው ለዚህ ነው ምክንያት ማወቅ ሚያስፈልገው። ሌላው ደሞ ሱባኤ ግዴታ በፆም ወቅት መሆን የለበትም ለብቻሽ ገዳም ሄደሽ መግባት ትችያለሽ ለአሁን ባይሆን ለቀጣይ ወር ትችያለሽ አመሰግናለው በርቺልኝ እህት አለም😊
Aug 01, 2024