#relationships Hello guys my question is for ORTHODOX WOMEN Ena endet new balachhun weym fkregnachhun bemenfesawi hiwotu handle mareg or meyaz yechalachhut/yemtchlut? Ene esu enen bemenfesawi hiwot wust meyaz alchalshm blo eskitazebegn dres blhat ansognal ena ebakachhu bezih bekul yale mtakutn yesetnet blhat astemrugn mknyatum ahun lalegn fkregna maletm wedefit lemagebaw bale tru menfesawi agarm mehon slemfelg new. Ena ketechale yene beteseboch strict nachew bzu endweta ayfekedlgnm kewetahum kesu befit mulu lifen update slemaregachew still endeza yfelgalu yhen consider argachhu share btaregugn des ylegnal kalhonem yalachhun jeba belugn. ena he is just my bf now for your information I'm 21 and he is 23. Thankyou.
Jul 31, 2024የመጀመሪያ ጉዳይ መንፈሳዊ ሕይወት የባልየው ሃላፊነት እንጂ ያንቺ ሃላፊነት አይደለም። የቤቱ ራስ ና ካህን ባል ነው። አንቺ የመደገፍ እንጂ እሱን የመምራት ሃለፊነት የለብሽም። ግን ገና ወደፊት ልትጋቡ ያላችሁ በመሆኑ እድለኛ ወንድ ነው ስለመንፈሳዊ ሕይወቱ የምታስብ ሴት ስላለው። የመጀመሪያ አንቺ ከእግዚአብሔር ጋር ያለሽ ሕይወት ይስተካከል ። በየቀኑ ቋሚ የጸሎት ስዓት ይኑርሽ። ብትቺዩ ጠዋት የመጀመሪያ ስራሽ ማታ የመጨረሻሽ ስራ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ አንብቢ በቋሚነት የንባብ ጊዜ ይኑርሽ። መንፈሳዊ መጽሐፍትንም አንብቢ ፤ ስብከቶችና ትምህርቶችን ተከታተይ youtube ላይ አለልሽ። በቤተክርስቲያን እና በሰንበት ትምህርት የሚሰጡ ትምህርቶችን ተከታተይ። የነፍስ አባትሽን ስለመንፈሳዊ ነገር አማክሪያቸው። በጸሎት ሰዓትሽ እንደ ርዕስ 1) እግዚአብሔር እውነተኛ ረዳት እንዲያደርግሽ ጸልዩ ፤ በመንፈሳዊ ሕይወትሽ እንድትበረቺ ጸሎትን እንድትለምጂ ፤ መንፈሳዊ ትምህርት እንዲገባሽ 2) እሱም በመንፈሳዊ ሕይወቱ እንዲበረታ አቅም እንዲሰጠው ጸልይለት 3) ወደፊት ባልሽ ሲሆን ፥ ባልነት ከባድ ሃላፊነት ስለሆነ እግዚአብሔር ለዚያ እንዲያዘጋጀው ፤ አንቺንም ለመልካም ሚስትነት እንዲያዘጋጃችሁ ጸልዪ
Aug 01, 2024