❗️❗️Sup aae❗️❗️ 12 Social result eyetebeku new ena yaw sigeba law nbr memar yefelekut ena silesu yeteleyayu info eyayew nbr ena min teredaw English betam asfelagi ende hone nw Esti law yemitimaru kalachu 1 and temari law lememar yegid perfect mehon alebet be English 2 min aynet exam nw yemitifetenut like mircha, derek tiyake,.. ? 3 Ende mibalew be tmhrtu grade ayseram? 4 eyetamarachut balachur tmhrt destegna nachu Lelam ngr chemrachu ngerugn ❗️❗️thanks❗️❗️
Jul 30, 2024⚖️ Law department 🔨 ትምህርቱ ሽምደዳ ሲሆን ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ከመጀመሪያ አመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጭ ያሉት የኮርሶች ፈተና open book ነው። 😄open book ማለት መምህሩ የሚፈቅድላችሁን ማንኛውም መፅሀፍ ይዛችሁ መግባት ትችላላችሁ። 🔨 ከዚህ በተጨማሪ የምትማሩዋቸውን ኮርሶች ማቴሪያል መፅሀፎች ከ መፅሀፍት ቤቱ ይሠጡዋችኃል። 🧑🎓ወደ ፈተናዎቹ ስንመለስ ከላይ እንዳልኳችሁ ከመጀመሪያ አመት ሁለተኛው ሴሚስተር ጀምሮ case ይሆናል የምትፈተኑት። ይህም ማለት የሆነ የፍርድ ቤት ክርክር አይነት ይሰጣችሁና ውሳኔውን እናንተው የምትሰጡት ይሆናል። 😏እዚህ ጋር የማልደብቃችሁ ነገር English language ሞካሪ መሆን ይጠበቅባችኃል። ምክንያቱም ውሳኔያችሁን ከ civil code አንቀፅ ጠቅሳችሁ ማብራራት ስለሚጠበቅባችሁ።ስለዚህ law መግባት ምትፍልጉ ልጆች የኢንግሊዘኛዋን ነገር አደራ 🫡 ⚖️Law department ለመግባት በመጀመሪያ ፍሬሽማን course 1st semester ትወስዱና then law and other social science ተብሎ 2nd semester ላይ ይከፈላል :: እዚህ ጋር ግን law መግባት ሚፈልጉ ተማሪዎች በCOC or በGPA ዉጤታችሁ ነዉ እንዲህ ሲባል አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች በGPA እና በentrance result ሲሆን ሌሎቹ ደሞ በentrance result እና በCOC ይሆናል :: ለምሳሌ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ COC የለም, entrance result 30% እና GPA 70% ተይዞ ከ50 ማይበልጡ ተማሪዎችን law ያስተምራል:: 🧑⚖️በመጨረሻም ከተመረቃችሁ በኋላ ለ 6 ወር ያክል የደሞዛችሁን ግማሽ እየተከፈላችሁ ለ 6 ወር ያክል ስልጠና ትወስዳላችሁ። ለምሳሌ አማራ ክልል ከሆናችሁ ባህር ዳር ትሰለጥናላችሁ። በመጨረሻም ዳኛ😎። ከቆይታዎች በኋላ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚያወጣውን የጠበቆች ፈተና ተፈትናችሁ ጠበቃ መሆን ትችላላችሁ።
Jul 31, 2024