Selam 12 tefetgnye yechereskugn negn ena le kremt short free online course that have certificate yet agegnyalew?
Jul 22, 2024#ጥቆማ በ2016 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚገቡ ተማሪዎች የተዘጋጀ ልዩ የህይወት ክህሎት ስልጠና ፕሮግራም ለአራተኛ ጊዜ #በነፃ ምዝገባው ከሐምሌ 16-23/2016 ዓ.ም ይካሔዳል። ያለው ቦታ ውስን በመሆኑ ቀድመው ለተመዘገቡ ብቻ ስልጠናው ይሰጣል። ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒውን እንዲሁም ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ እንደነበራችሁ የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ቤታችሁ በማፃፍ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል። የሚሰጡ ስልጠናዎች፦ ► የአመራር ክህሎት / Leadership Skills ► የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ /Entrepreneurial Mindset ► ዲጂታል ማርኬቲንግ / Digital Marketing ➤ ግራፊክስ ዲዛይን / Graphics Design ➤ ፕሮግራሚንግ 1 (ፓይተን) / Programming ስልጠናውን በሚገባ ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ሰርተፍኬት ይሰጣል። ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ የተመረጡ ተማሪዎች #ነፃ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ተመቻችቷል፡፡ አድራሻ፦ መካኒሳ / ጀሞ ሚካኤል ከአፍሪካ ህንፃ አጠገብ ☎️ 0113854042 / 0904848586 Website፦ https://kibur.net Telegram፦ https://t.me/kiburcollege Facebook፦ https://www.facebook.com/kiburcollege #kiburcollege #highschool #training
Jul 23, 2024