Selam indet nachu f negn Ina my questions is letidar or lequmineger lefuture abiro lemenor legabicha min ayinet wond nw mehon yalebet I mean that it may be his behavior, ethics his profetion so on please hasabachun nigerugn
Jul 20, 2024ለትዳር ለቁምነገር ለፊውቸር አብሮ ለመኖር ለጋብቻ . . . በመጀመሪያም በመጨረሻም ሰው ነው የሚያስፈልገው። ሰው ደግሞ በሚሞት ሥጋው ውስጥ የማትሞት ሕያው ነፍስ የተቸረ እንደመኾኑ ሥጋዊ ነኝ ብሎ ለሥጋው ብቻ ሳይል መዋቲ ሕያው ነኝ ብሎ ለነፍሱም የሚኖር ፍጥረት ነው። የትዳር አጋር ሲኾን ደግሞ ለዚኽች ሕያዊት ነፍሱ እና የነፍሱ ነጸብራቅ ለኾነች ለሌላኛው ነፍሱ ( ሚስቱ ) የሚተጋ መኾን ይገባዋል። ቢያበላት ቢያጠጣት ያማረ አልጋ ላይ ቢያስተኛት ምን ምን ምን 70ዘመን ነውና ሺኅ ዓመት እንደ አንዲት ቀን ብርሃንን ተጎናጽፋ በአኰቴት ይኖሩ ዘንድ ለሰማያዊው ክብር ተግቶ የሚያተጋት ቢኾን ይመረጣል። ለሴትም ያው ነው።
Jul 21, 2024