በጣም የማፈቅራት ፍቅረኛ አለችኝ አንድ ዓመት የፍቅር ግንኙነት አለን ነገር ግን ከእሷ ከ3 ዓመት በፊት ጀምሬ በቴሌግራም &Fb የማዋራት ውጭ ሀገር የምትኖር ሌላ ልጅ አለች በጣም ነው የልቧን ገልጻ የምታዋራኝ ለሊት ላይ ሁሉ በቪድዮ ኮል እናወራ ነበር ውጭ ሀገር ለምትኖረው ልጅ በተዋወቅን በዓመታችን የፍቅር ጥያቄ አቀረብኩላት ነገር ግን እሷ ዝምብለን እንድናወራ ወንድም ጓደኛ እንድትሆነኝ ነው የምፈልገው ሌላ አልፈልግም አለችኝ በቃ እሽ ብየ ጓደኝነታችንን ቀጠልን እኔም ከእሷ ጋር ተስፋ እንደሌለኝ ሳውቅ ሌላ የፍቅር ህይወት ጀመርኩኝ ግን ከእሷ ጋር ያለኝን ወሬ ምናምን አላቆምኩም። አሁን ከሳምንት በፊት በጣም እንደምታፈቅረኝ ከ2 ዓመት በፊት የጠየከኝን የፍቅር ጥያቄ ልቀበልህ እፈልጋለሁ ወደ ሀገርቤት ልመጣ ስለሆነም እንጋባለን አለችኝ። ልትመጭ ነውንዴ ምናምን ብዬ በወሬ አለፍንው እኔ እሷ እምቢ ስትለኝ ወደሌላ ግንኙነት ገብቻለሁ ነገር ግን እሷ በቃ እስካሁን እያዋራኋት ስለሆነ እየጠበኳት ነው የመሰላት በጣም የማፈቅራት ልጅ እንዳለችም አታውቅም። ከእሷ ጋር እንዳለኝ ቅርርብነት ፍቅረኛዬ ጋርንኳ የለኝም በአካል ሳንተዋወቅ በቪድዮ ብቻ በጣም ተላምደናል ፣ ብነግራት ትጎዳለች ብየ ፈራሁ ምን ይሻለኛል?
Jul 20, 2024Btam mtkrarbu khone endat sle fkregnak eskahun alngerkatm.......it seems tesfa kortku alk enji alkortkm nber
Jul 20, 2024