ጥንቃቄ ለወላጅችና ለወጣቶች ‼️ ኢትዮጵያ ውስጥ የIT ተማሪዎች የሆናችሁ ልጆች ወደ ታይላንድ ስራ አለ በማለት ኢንተርቪው አድርጋችሁ ሌሎችም ዶክመንት አቅርባችሁ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ በሙሉ ጉዟችሁን እንድትሰርዙ:: እስካሁን በቁጥር የማይታወቁ ኢትዮጵያዊያን ይህን ዶክመንት አሟልተው ከሄዱ በኃላ ወደ ማይናማር ታግተው መወሰዳቸውን እና እዛ በጉልበት የተለያዩ የኦንላይ ስራዎችን ሃኪንግ ጨምሮ እየሰሩ ይገኛሉ:: እነዚህን ወጣቶች ቤተሰብ ለማስለቀቅ በኢትዮጵያ ከ500 ሺህ ብር እስከ 750 ሺህ ብር ድረስ በመክፈል ላይ ይገኛሉ:: ይህን ጉዳይ የሚሰሩት ደግሞ ሃበሾች መሆናቸው እጅጉን ያሳዝናል ያበሳጫልና በማይናማር በዚህ ህገወጥ ስራ የተሰማሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ታግተው ገንዘብ ተከፍሎ ከተመለሱ ሰዎች አአጋግጫለሁ:: በአሁን ሰአት እኔ የማውቃቸው ሰዎች ልጆችም በማይናማር ታግተው እስከሁን 300 ሺህ ብር ከፍለው ልጆቻቸው እንዲለቀቁ በመጠባበቅ ላይ ናቸውና ጥንቃቄ አድርጉ! https://t.me/NatnaelMekonnen21
Jul 20, 2024