hey endet nachihu e personally beka yesewoch ngr yikebdegn nbr btm ahun ahun gn betam chekagn eyehonku nw bka wede mefthew nw mehed mfelgew malet yihe mazen mnamn milew ngr teftobgnal ena thats hard libe dendana hone yihe degmo kebad nw so pls endet limeles
Jul 16, 2024ሰላም! በመጀመሪያ ይህ ስሜት እንዳለ ማመን እና ምክር ለመቀበል ፈቃደኛ ሆኖ ራስን ማቅረብ የሚደነቅ ነገር ነው! ቀስ በቀስ ያለንን አዛኝነት እንድናጣ የሚያደርጉን ነገሮች በጊዜ ሂደት የሚያጋጥሙን አጋጣሚዎችና የምናልፍበት ልምምድ ነው! ያጋጠሙን ሁኔታዎች አመለካከታችንን የመለወጥ አቅማቸው ቀላል አይደለም ይህን በምሳሌ ለማስደገፍ ...ልጅ እያለን ስለ ዓለም የነበረን አመለካከትና እይታን ማንሳት እንችላለን! የሚያሳስበን ነገር በጣም ውስን እና ምናልባትም አሁን ላይ ትልቅ ሆነን ስናስበው እዚ ግባ የሚባል እንኳ ያልሆነ ሃሳብ ይሆናል፤ ብዙ ነገር የምናሳካ፣ ትልቅ ቦታ የምንደርስ፣ ነገሮች አልጋ ባልጋ የሚሆኑልን መስሎን ነበር! Realityን መኖር ስንጀምር ግን እውነታውን ሌላ ሆኖ አገኘነው አይደል! ነጥቡ ምንድነው ለሰዎች ቀና ማሰብ፣ መልካም ማድረግ፣ መራራት፣ የተቸገሩትን መርዳት ከልጅነታችን ጀምሮ ውስጣችን ያለ ነገር ሲሆን በምናድግበት ሃይማኖታዊ አስተምሮም የምንመከረው ነገር ነበር! በጊዜ ሂደት ግን የሰዎችን ችግር ሙሉ በሙሉ መፍታት እንደማንችል ስንገነዘብ አቅመቢስ እንደሆን ስለሚሰማን ያንን ስሜት ልንሸሸው እንችላለን! አሊያም መልካም ያደረግነው ምላሽ ጠብቀን ባይሆንም ያገዝናቸው ሰዎች ምስጋና ቢስ ሲሆኑ፣ መጠቀሚያ ሲያደርጉን አለፍ ሲልም መጥፎ ድርጊት ሲፈፅሙብን መልካም መሆን በቃኝ ብለን ልንወስን እንችላለን ወይም ደግሞ ሰዎችን ለማገዝ ስንሞክር ያጋጠመን መጥፎ አጋጣሚ (ለምሳሌ: ወንጀል ተፈፅሞብን) ከሆነ ርህራሄን ከዛ በኋላ ማሳየት ሊከብደን ይችላል። ዓለም እንደዚ ናት! አውቃለሁ አምኖ ለመቀበል ከባድ ነው ግን ጥሩነት እና መልካምነት ሁልጊዜ አያሸንፉም! አንድ ወዳጄ የመከረኝን መቼም ከአዕምሮዬ የማላወጣውን ሀሳብ በማካፈል ላብቃ! ሁሌ ሰዎች ለምን ክፉ ይሆናሉ በሚል እርስ ስንነጋገር ከቆየን በኋላ “የአንድ እኔ ጥረት ብቻ እዚህ ግባ የሚባል ለውጥ እኮ አያመጣም” የሚል ሃሳብ ስሰነዝር የሚከተለውን አለኝ “በጨለማ የተሞላን ክፍል ለማብራት 1 ሻማ መለኮስ ይበቃል፤ ለውጥን፣ የተሻለ ዓለምን እና የተሻለ ማህበረሰብን ከፈለግክ አንተ እንደ ሻማ እየቀለጥክ አብራ! አንተ ብትቀልጥም የብርሃንን ምንነት በማሳየት ተስፋን አሰንቀህ እለፍ” 🙏
Jul 16, 2024