ኣረ ሰዎች ድረሱልኝ ድረሱልኝ ከ2 አመት በፊት ነው እንዲህ አይነት ስሜት የተሰማኝ ድፍን 2 አመት ማንንም ሰው ከማንም ሰው የአይን ፍቅር አልያዘኝም..!! ሱቅ ውስጥ ነው የምሰራው...ሳልፈልግ እሱን እንዳላይ አንገቴን እየደፋሁ ነው። አይናችን የትም ከረገጠ በኋላ ዞረን ተፋጠን ከርቀት እንተያያለን በምልክት ሁሉ እናወራለን እንሳሳቃለን ረጅም ሰዓት ስልክ ሳወራ አይወድም ያልገባኝ አብረውት የሚሰሩ ሰራተኞች ሁሉም እኔን ይከታተሉኛል ስላችሁ በየቦታው ያሰማራቸዋል ነገር .. እኔም ወደ እነሱ ሳንጋጥጥ እነሱም ሲያንጋጥጡ እኩል እንጋጫለን። የሆነ ሰዓትማ እሱ እኔን እቃ ዝም ብሎ መግዛት አብዝቶ ነበር እና የእቃውን ስም አሳሳቶ ነው የሚነግረኝ ከዛ ይህን ማለቴ ነው ይላል..ቀና ብሎ አይኔን ማየት አይችልም። እንደዚህ አይነት ስሜት ለማንም እንዳይሰማኝ በጣም ተጠንቅቄያለሁ....እባካችሁ 1 ነገር በሉኝ ምንም የፍቅር አይነት ስሜት እንዲሰማኝ አልፈልግም ...ሀሳብ አስቀምጡ እስቲ..ትላንት የአይን ፍቅር እንደያዘን ሳናውቅ በፊት መተያየት ኖርማል ነበር ዛሬ ግን ሀጥያት ሆነ...የሚበጀውን መፍትሔ እጠብቃለሁ !?
Jul 15, 2024Gurl tf jus give him a chance ezegni eski
Jul 15, 2024