ሰላም ወንድም እህቶቼ በስላሴ ትምህርት ላይ አንድ ጥያቄ ነበረኝ! እግዚአብሔር በ አካል ሶስት በ አምልኮ አንድ ከሆነ አንድ አምላክ አለን ነው ሚባለው! እና እሺ በመጨረሻው ዘመን እግዚአብሔር ፍርድን ለመፍረድ ሲመጣ በአካል ሶስት ስለሚል ሶስት ሆኖ ነው ሚመጣው???? እስቲ የምታውቁ እህት ወንድሞቼ በደንብ አስረዱኝ የዚን ጥያቄ መልስ እና ይሄ ልጅ ማወቅ አለበት የምትሉትን አጠቃላቹ
Jul 13, 2024በአጭሩ በአካል 3 ሲባል እኛ ምናቀው እጅ እግር ያለው ገጹን ማየት የምንችለው የሚዳሰስ ማለታችን አይደለም...አብ የራሱ ልዩ ገጽ ወልድ ልዩ ገጽ መንፈስቅዱስም ልዩ ገጽ አላቸው ሲል ነው...ወልድ በተለየ አካሉ ከአብ ከወልድ ሳይለይ ስጋችንን ስለነሳ ልናየው ችለናል...በእርሱ በኩል አብን እና መንፈስቅዱስን ማየታችን ሳይዘነጋ ማለት ነው...ስለዚህም እኔ የተማርኩት በዳግም ምጽአት ጊዜ የምናየው ወልድን በስጋ እንደሆነ ነው ምክኒያቱም የሚታይ ስጋን ስለለበሰ እንጂ ከአብ ከመንፈስቅዱስ በባህርየ መለኮቱ አንድ ስለሆነ በዛ መልኩ አናይም...ባህርየ መለኮትን ማየት መቋቋም ስለማንችል "እነሆ ከደመና ጋራ ይመጣል የወጉት ሁሉ ያዩታት። ራዕ 1:7"
Jul 14, 2024