ሰላም እንዴት ናቹ ጓደኞቼ አንድ ነገር ላማክራቹ ነበር የሆነ ዘመድ ነገር አለን እና ለኔ ስኮላር እየሞከርልኝ ነው እናም በሰበቡ መገናኘታችን አይቀርም ግን ስንገናኝ በቃ አቅፎ አንገቴም ጉንጬን ይስመኛል አልፈልግም እለዋለው ግን እሱ ደሞ ምንም አስቦ እንዳልሆነ እና እኔ ምን አደረኩሽ ነገር አይነት ይለኛል በእውነት ነው ምላቹ እሱ እንደዛ ሲል እኔ ነኝ እንዴ ጥፋተኛ ብዬ እራሴን እጠይቀዋለው ዛሬ ግን በቃ ይሄንን ሲደግመው እንደውም ስኮላሩን አልፈልግም ትቼዋለው አልኩት። እኔ ምንም የምተማመንበት ሃብትም ሆነ የናጠጡ ቤተሰቦች የሉኝም አውቃለው ግን ህሊናዬ እንቢ አለኝ። ገላዬን መሸጥም ባንለው አዳርቼው የማገኘው ያህል ተሰማኝ። ለሱ አልፈልግም ስለው ይሄን ያህል እኔ ምን አርጌሽ ነው ክፉ ሰው ነኝ ወይ ከፈለግሽ ይቅር አለኝ። አሁን ያስጨነቀኝ ለቤተሰቦቼ ምን ብዬ እንደማወራ ነው? ዝምድናው ለአባቴ ነው እናም ከቤተሰብ ጋር በጣም ይቀራረባል። ተውኩት ለማለት ምን ምክንያት ልስጥ? እኔ እውነቱን ተናግሬ ቅራኔም መፍጠር አልፈልግም። የማንንም ጥፋት አንስቼ ሰውን ማስወቀስም አልፈልግም እሱን ለፈጣሪ ትቼዋለው ህሊናው ይውቀሰው ግን አሁን ምን አይነት ሰበብ ነው የምሰጠው እስኪ መላ በሉኝ በእግዚአብሔር
Jul 12, 2024Yene konjo yetgawem ye hiwotish kefel west yemayker Neger nw ahun yagatemesh bene bekul esuga setheji bechashen atehiji enji yejemrshewn atakuarchi bay neg kezam yebase sent ale bechalshew akem kezi Hager wechi aderashen🙌
Jul 12, 2024