ሰላም ቤተሰቦች ለኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ጥያቄ ላቅርብላቹ ከዚክ በፊት ፆም ላይም ይሄንን ያክል አይደለሁም እና ከሰሞኑ 1የቤተሰብ ችግር ገጥሞኝ ነበር እና በዚህ ሰዐት የአባቴ ወንድሞች ማለትም አጎቶቼ ከአባቴ ጎን ለመቆም አልፈለጉም ይህ ደግሞ የወደፊት ህልውናችን ነው እና ቤተክርስቲያን ስለት ለመሳል ነበር ግን ከመሳሌ በፊት ይህንን አድርግ ስለትህ እንዲደርስ ምትሉኝ ካለ እባካችሁ
Jul 11, 2024ስለት በመሰረቱ እንደ ሰው ይለያያል እግዚአብሔር ኃጢአተኛ ሆንክም አልሆንክም ይሰማል ስለዚህ የአንተ ስራ የሚሆነው አልቅሰህ እግዚአብሔር ከልብህ መጠየቅ ነው።ግን ስለትህን ሁሌ እንደተለመደው ገንዝብ፣ጧፍ... ምናምን አታድርግ በራስህ ላይ ለመሳል ሞክር ለምሳሌ የማትጾም ከሆነ ከዚህ በኋላ እንደምትጾም ለእግዚአብሔር ቃል ግባ ምክንያቱም እግዚአብሔር ከገንዘብ ይልቅ የእኛን መመለስ ይፈልጋል።እና ደግሞ ሁሌም ስለት ላይሰምር ይችላል ይህ የሚሆነውም እግዚአብሔር በሚያውቀው ነገሩ ለእኛ የማይጠቅም/የማያስፈልግ ወይም የሚጎዳን ከሆነ አልያም በሌላ ምክንያት ላይሰምር ስለሚችል ቶሎ ተስፉ አትቁረጥ።
Jul 12, 2024