Selam tnsh gera yegebagn teyake neber eski yemtawku melsulgn Tewahedo,Qibat,sost lidet leyunetachew mnden nw?
Jul 10, 2024ቅባት እና ጸጋ Ethiopia closed door policy (ምንም አይነት የውጭ ሀገር ግንኙነት ማቋረጥ) የሚባለውን መከተል ስትጀምር በወቅቱ የነበረው ንጉስ ሀገሪቷ ላይ ያሉትን የውጪ ዜጎንችን አስወጥቶ ነበር እናም የዛን ጊዜ የነበሩት የካቶሊክ ሚሲሆኖች ለ 2 የተለያዩ ሰዎች ምንፍቅናን አስተማራቸዉ ለአንዱ ቅባት (ድንግል ማርያም ክርስቶስን የወለደችው ከስጋዋ ስጋ ከነፍሷ ነፍስን ነስቶ ሳይሆን የሰዉ ልጅ ቅባትን ከቆዳው በላይ እንደሚቀባው ሁሉ ክርስቶስንም ተቀብታዉ ነዉ ይላሉ) ጸጋም ደሞ እንደ ጸጋ ለብሳው ነው ይላሉ ተዋሕዶ ግን ከስጋዋ ስጋን ከነፍሷ ነፍስን ከ አብራከ መንፈስ ቅዱስ ወለደችው እንላለን:: በአፄ ዮሐንስ 4ተኛ (ከ አፄ ምኒሊክ በፊት የነገሰው) ዘመን በአንድ ሀገር ውስጥ ኣንድ ሀይማኖት ብቻ መኖር አለበት ሲል የ3ቱንም ሀይማኖቶች ሊቃውንት ጠርቶ በቦሩ ሜዳ ተሟግቶ ያሸነፈ ብሔራዊ ሀይማኖት እንደሚኖራቸው ነገራቸው ከዛም አባቶቻችን ተሟግተዉ አሸነፉ በመሆኑም ተዋህዶ ብሔራዊ ሀይማኖት እንዲሆን ታወጀ ይሄ ሁሉ ይሁን እንጂ አሁንም አሉ በ ኦርቶዶክስ ስም በተለይ በጎንደር እና በጎጃም አካባቢ አሁንም አሉ።
Jul 11, 2024