ኧረ እባካችሁ ስለ Thailand ስራ የሆነ ነገር በሉን ብዙ ሰው እየሄደ ነው ያለው
Jul 10, 2024ደላሎችም ይሁኑ ' ወደ ውጭ ሀገር እንልካችሏለን ' የሚሉ ኤጀንሲዎች የት እና ለምን ስራ እንደሚልኳቹ በደንብ አጣሩ !! ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ወጣቶችን " ለብሩህ ተስፋ፣ ለጥሩ ህይወት ጠቀም ያለ ገንዘብ የሚያስገኝ ስራ በታይላንድ አለ " በማለት ወጣቶቻችንን ለከፋ የስቃይ ህይወት የሚዳርጉ ሰዎች አሉ። አንዳንዶቹ ጭራሽ ወደ አሜሪካ ፣ ካንዳ እና አውሮፓ ሀገራት ነው የምንልካችሁ በማለት የሚያጭበረብሩ ናቸው። በእነዚህ ደላሎች እና ኤጀንሲዎችም ጭምር ተታለው ታይላንድ ተብለው የሚሄዱ ሰዎች እጅግ አስከፊ ስቃይ እና ዓለም አቀፍ የማጭበርበር ወንጀል ወደ ሚሰራበት በታይላንድ አቅራቢ ወዳለችው ማይናማር (ድንበር ላይ) ወዳለ ካምፕ ያስገቧቸዋል። ይህ ሁሉ የሚሆነው በኃይል ነው። ታይላንድ የደረሱ ወጣቶች ገና ኤርፖርት ላይ ሲደርሱ ተቀባይ አላቸው። " እፎይ አሁን ህይወታችን ሊቀየር ነው ወደ ሆቴል / ወደምንሰራበት ስፍራ ሊወስዱን ነው " ብለው ሲጠብቁ ከከተማ ውጭ በተቃራኒ መንገድ በመኪና ረጅም ጉዞ ያስጉዟቸውና ወደ አደገኛው የማፍያዎች ስፍራ ያስገቧቸዋል። እነዚህ ቦታዎች የደህንነት ካሜራ ገና ከበር ጀምሮ ያላቸው፣ መሳሪያ በታጠቁ ሰዎችም የሚጠበቁ ሲሆኑ ማፍያዎቹ ወጣቶቹን በማስገባት ህገወጥ ስራ እንዲሰሩ ያስገድዷቸዋል። ይኸው ህገወጥ ስራ ዓለም አቀፍ የሆነ የኦንላይን የማጭበርበር ስራ ነው። ወጣቶቹ በይቆታቸው ፦ - አሰቃቂ ድብደባ ይደርስባቸዋል፣ - ምግብ ይከለከላሉ፣ - ሴቶች ይደፈራሉ፣ - ማሰቃየት (በኤሌክትሪክ ሾክ) ይፈጸምባቸዋል፣ - በሰንሰለት ይታሰራሉ፣ - በኤሌክትሪክ ሽቦ ይገረፋሉ። እስከ ግድያም ሊደርስ ይችላል። ህይወታችን ይቀየራል ብለው ከፍተኛ ዋጋ ከፍለው የሄዱ ወጣቶች ለወራት አንድም ብር ሳያገኙ ጭራሽ ህይወታቸው በስቃይ ይሞላል። እድለኞች ከብዙ ስቃይ በኋላ ይወጣሉ። አሁንም የውጭ ሀገር ፕሮሰስ እያደረጋችሁ ያላችሁ የሀገራችን ልጆች የት ? ለምን ? ስራ እንደምትሄዱ ጠይቁ መርምሩ። አሁን ላይ በማይናማር እና ታይላንድ ድንበር በሚገኝ ስፍራ እንደ ባርነት የተያዙ የበርካታ ሀገራት ወጣቶች አሉ። ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሚመለከተው አካል ይህን ጉዳይ ተከታትሎ እንዲደርስላቸው ተማጽነዋል። ታይላንድም ይሁን አሜሪካ ፣ ካናዳም ይሁን አውሮፓ ደህንነቱ የተጠበቀ ህጋዊ ስራ ካልሆነ ባትሄዱ ይመከራል። የሚልኳችሁን ሰዎች በትክክል የት ነው የምንሄደው ? የምናርፈው የት ነው ? የድርጅቱ ስም ምንድነው ? የመስሪያ ፍቃዱ የታለ ? አድራሻው የታለ ? ከዚህ በፊትም የሄዱ ልጆችን አገናኙን ብላችሁ ጠይቁ። #TikvahEthiopiaFamily @tikvahethiopia
Jul 10, 2024