ለሴት ልጅ ማድረግ ያለብኝ ነገር ሁሉ በቻልኩት አቅም አደርጋለሁ። ሁሌ ሲጎዱ ሳይ ፊቴ የምትመጣው እናቴ ናት። እና በዚህ ምክንያት ከራሴ ካለኝ ጊዜ ላይ ለመስጠት አልሳሳም። እና ብዙ ጊዜ ራሳቸው ናቸው የሚያወሩኝ። ነገር ግን፣ አብዛኛዎቹ እንዳፈቀርኳቸው ስለሚሰማቸው ይኹን ባላውቅም ከመሬት ተነስተው ቻት ያጠፋሉ። እና ይሄንን ከ1ም ብዙ ጊዜ ተመልክቻለሁ። ድንገት ዝም ካልኩኝ መኩራትህ ነው? አንተ ከማንም አትበልጥም እሺ ይሉኛል። እውነታው ግን ሰዎች ቢከቡኝም ብቸኝነት ስለሚሰማኝ ነው። እና አሁን ያሰብኩት ነገር ሴት ከሚባል ሁሉ መራቅን ነው። ምክንያቱም ምንም ልረዳቸው አልቻልኩም። የተረፈኝ ነገር ሕመምና ጭንቀት ብቻ ነው። እና ምን ይሻለኛል ይሄ ሃሳቤ መልካም ነውን?
Jul 09, 2024Welcome to the singles ጀመአ ብለናል
Jul 09, 2024