ሰላም ታግሳቹ ስለምታነብ አመሰግናለው በተለይ psychiatrist ካላቹ እንድትነግሩኝ እፈልጋለሁ?, ከ ዛሬ6 አመት በፊት በ 18 አመቴ ነበር የፍቅር ግንኙነት የጀመርኩት እና በጊዜው ለ 1 ዓመት ጥሩ ጊዜ ነበረን ከዛ እሱ ተመረቀ እና ወደ ሌላ ከተማ ለስራ ሄደ እኔም ወደ ግቢ ገባው ግን ግንኙነታችን ቀጥሎ ነበር arrange አድርገን እንገናኛለን , ከዛ አሁንም ከ2 አመት ቦሀላ ወደ ውጭ ሀገር ሄደ እና ባህሪው ተቀየረ ሁልጊዜ ጭቅጭቅ አበዛ ቅናት ምናምን ፣ ሰላም አሳጣኝ እና እኔ በጓደኞቼ ግፊት አሳውቄው አቆምኩ፤ ከዛ ግን እንዳሰብኩት ልረሳው አቻልኩም እና ተመለስኩ ግን ስቲል ታማኝ ነበርኩ ፤ እና በመሀል ወሬ ሰማው እና ሳጣራ እውነት ሆነ ፣ ስጠይቀው አመነ ማግጦ ነበር ውጪ ከመሄድ በፊት እና የአንድ ቀን ስተት ነው,ያለፈ ጊዜ ነው ይቅርታ አድርጊልኝ ቢለኝም አልቻልኩም፣ አልፈልግም ብዬ ተለያየን ከ 4 አመት ቆይታ እና ብዙ መስዋዕት ከከፈልኩ በሀላ ፣ ግን ከተለያየን 2 አመት አለፈ ሌላ ሰው date አደርጋለው ግን ምንም ደስተኛ መሆን አልቻልኩም ፍቅርም ሊይዘኝ አልቻለም፣ አሁን 24 አመት ሆነኝ። ፣ እስከ ቅርብ ጊዜ እሱም እንድታረቀው ሲጠይቅ ነበር ፣እንቢ አልኩ ግን ደግሞ ከሌላ ወንድ ጋርም መሆን አልቻልኩም ፣በዚው ከቀጠልኩ ቆሜ መቅረቴ ነው ፣ ሀሳብ ስጡኝ እስቲ ምን ላድርግ ?እንዴት ወደ ኖርማል ሕይወት ልግባ?
Jul 07, 2024Cheating is NOT a mistake. Move on with ur life, ayzosh it'll pass and you'll heal 😊
Jul 07, 2024