"መስከር እንጅ መጠጣት አልተከለከለም ..."!? 1- የሚጠጣው መጠጥ በራሱ ስያሜው "አስካሪ መጠጥ" ነው፡፡ በመጀመሪያ መጠጡ ዋነኛ ግቡ ማስከር ነውና እሱ ስራውን ይሰራል..! ይህችን ፁሁፍ ጋ ስደርስ ሰክረህ እንኳን ቢሆን ፈገግ ትላለህ ምክንያቱም እንደዛ እንደማይሆን ሁላችንም እናቃለን፡፡ 2- ማንኛውም ሰው መጠጥ መጠጣት እንጀመረ የስካሩ መጠን ይለያይ እንጅ መስከር ይጀምራል፡፡ መጠጡ ከተጀመረ በጣም የመስከርና ጥቂት የመስከር እንጅ "ያለመስከር" የሚባል መለኪያ የለውም፡፡በጣም የሚያሳዝነው እንደ ቅርብ ጊዜ ጥናቶች መሠረት ጥቂት እንኳን መቅመስ የካንሰር በሽታን ያፋጥናል፡፡ በጣም ጥቂት እንኳን ..! ይህንን መረጃ መመልከት ይችላሉ! 3- ባይብል ውስጥ "መጠጥ ይፈቀዳል" የሚል ቃል አታገኙም በተቃራኒው ብዙ ቦታዎች ላይ ሲከለክል ግን እናያለን ለአብነት (ኤፌሶን 5:18) (1ኛ ጢሞቲዎስ 3:8). (ቲቶ 2:3) ወዘተ 4- እምነት ማለት ከስሜት በመቃረን ለሚገኝ መንፈሳዊ ደስታ መትጋት እንጅ እምነትን አዋርዶ ስሜትን ማስደሰት አይደለም፡፡
Jul 07, 2024Yetekeskachew tksoch andachewm aykelekelum so atwash mejemerya lelaw gn mesker new enji metetat altekelekelem masreja kaleh bemasreja awra
Jul 07, 2024