✧══════•❁❀❁•══════✧ ሀሀርኤል ✧══════•❁❀❁•══════✧ በሚኪያስ (MikoPia) 🔴ክፍል ፬ . . .49 ምዕራፍ የሚኾን አስጨናቂው የጨለማ ጉዞዬ ! በድቅድቅ ጨለማ ስለተመላው 49ምዕራፍ ስለሚኾነው ጉዞዬ ሳስብ በአረጋዊው ብርሃንነት የተመለከትኳቸው በየሰባት ምዕራፉ በደም የተሞሉት ሰባት ጽዋዎች ከዓይነ ሕሊናዬ የማይጠፉ ነበሩ ። ከእነዚኽ ጽዋች ሞልቶ የሚፈስሰው ደም በጨለማ የተመላውን የዋሻውን መሬት ከማራሱ በላይ ጠረኑንም ቀይሮታል ። ትኩስ ደምን ትኩስ ደምን የሚሸትት የጨለማ ዋሻ ነበረ ! እነዚኽ ሰባት ጽዋዎች ምን አልባት መሲሁ ከመምጣቱ አስቀድሞ ሰይጣንን ከሙሉ እስራቱ የሚያስለቅቁና ሦስት ዓመት ተኩሉ መነሻ ሦስት ዓመት ተኩሉ አደገኛ እልቂት የሚያስከትለውን ሰይጣን ከአየር ውስጥ አስወግዶ ወደ ምድር የሚያስጥሉ ይኾኑ ? ወይስ ባለራዕዩ እንደገለጸልን ተፈጽሟል የሚል ታላቅ ድምጽን ከዙፋኑ እንዲወጣና ሰባቱ መላእክትን በአየር ውስጥ አድርጎ ሰባት የቁጣ ጽዋዎችን ወደ ምድር እንዲያፈሱ የሚያደርጉና የእግዚአብሔርን የቁጣ ቀን አመላካች ይኾኑ ? በመጀመሪያው ጽዋ ውስጥ የኹለት ታላላቅ አረጋዊያን የራስ ቅሎች ተቆርጠው በደሙ ላይ ይንሳፈፉ ነበረ ! . . . . ሚኮጵያ ✧══════•❁❀❁•══════✧ ቀን ይወጣል ብዬ ብጠብቅ ባስጠብቅ እንኳን ቀን ሊወጣ ጨለማ ነው ድቅድቅ። ✧══════•❁❀❁•══════✧
Jul 06, 2024