ሰላም ሰላም ቤተሰብ በጣም የተጨነኩበትን ነገር ላካፍላችሁ እና any one help me out as much as you can pls ወንድ 21 አመቴ ነው ቅዳሜ እና እሁድ Uv እየተማርኩ ነው በግል እና ወላጆቼ ናቸው የሚያስተምሩኝ እስካሁን የኔ የምለው ነገር የለኝም ለሻይ የሚሆን ብር እንኳ የማይኖርበት ጊዜ ይበልጣል ጓደኞቼ ከኔ የተሻለ ነገር አላቸው የግል ስራ ..bla bla እና እኔ በ ሁሉም ነገር ስኬታማ ሰው መሆን እፈልጋለሁ ብዙ ነገር ላይ Active ነኝ ነገሮችን ቶሎ እረዳለሁ ማንኛውንም ስራ ቶሎ ይገባኛል ሁሉንም ማድረግ እችላለሁ አሁን ያለብኝን ችግር መቅረፍ እፈልጋለሁ በተለይ ደሞ የገንዘብ ችግር ለዚህ ስል ደሞ ምንም ቢሆን ለማድረግ ዝግጁ ነኝ የተሻለ እድል ከሆነ ምንም ነገር ለመተው አላመነታም የኔንም የቤተሰቤንም ህይወት መቀየር እፈልጋለሁ ፋዎል እንኳ ቢሆን ከመስራት አልመለስም😥ትመህርት እስክጨርስ የምታገስበት ሁኔታ ውስጥ አይደለሁም ስራ መስራት እፈልጋለሁ ሊረዳኝ የሚችል ሰው ካለ እባካችሁ እርዱኝ i am getting to deep depression እፀልያለሁ ግን አልቻልኩም በቃ እርዱኝ
Jul 04, 2024እንደኔ የምመክር ራስህን ከጓደኞችህ ጋር አታወዳድር እነሱ ስራ ስለያዙ አይደለም መስራት ያለብህ እሺ።ቅዳሜና እሁድንም ተማር ጥሩ ነው ግን ግን ብዙም ለገንዘብ አትጨነቅ ማለቴ ገንዘብ ለማግኘት ይሄን ያህል በጣም ድባቴ ውስጥ እስክትገባ አትጨነቅ እሺ።...ካልሆነ ይሄን ያህል ገንዘብ ለማግኘት የምትጨነቅ ከሆነ ወደ ገንዘብ ፍቅር ይቀየርብህና ይህ የገንዘብ ፍቅር ደሞ ወዳልሆኑ ህገወጥ ገንዘብ ማግኛ ነገሮች ሊመራህ ይችላል። የስራ መስራት ፍላጎትህ ጥሩ ነው ግን እ ምን መሰለህ ለገንዘብ አትጨነቅ ቀፋፊ ነው ሲያስፈልግህ አትጣ እንጂ...በሚያስፈልግህ ጊዜ ብታጣ ራሱ ልታገኘው የምትችለው ነገር ነው ካገኘኸው በዃላም የምታጣው ነገር ነው። እና ምን ልልህ ነው በአጭሩ በአጭሩ ስራ እንድታገኝ ፈጣሪ ይርዳህ ግን ግን ለገንዘብ ማለቴ ገንዘብ ለማግኘት እንዲ depression ውስጥ እስክትገባ ድረስ ብዙም አታስብ ለማለት ያክል ነው።
Jul 04, 2024