Selam indet nachu Corrupted kehone memory photo recover mareg michalibet menged kale nigerugn isti
Jul 03, 2024በሚሞሪ ካርድ ሪደር ኮምፒውተር ላይ ሰክተው ይክፈቱት። ሞባይል ላይ ያላነበበ ሚሞሪ ኮምፒውተር ላይ ሊያነብ ስለሚችል። ከከፈተና ፋይሉን ካሳየ ኮፒ አድርገው የሚፈልጉትን ወደ ኮምፒውተሩ ይገልብጡት። 👉ኮምፒውተር ላይ የማያነብ እና ፎርማት አድርግ የሚል ሚመጣ ከሆነ ፎርማት ሳያደርጉት የተለያዩ ሪከቨር ቱልስ ሶፍትዌር (minitool recovery, esaeus recovery ...) የመሳሰሉ ከ Getintopc.com ላይ ዳውንሎድ አድርገው ኮምፒውተር ላይ ጭነው ከፍተው ሚሞሪ ካርዶን በመምረጥ ስካን ያድርጉና ይሞክሩ። ፋይሉን በሪከቨሪ ቱል አማካኝነት ስካን እያደረገ የሚያሳይ የሚያመጣ ከሆነ ከዛው ከቱሉ ወይም ሶፍትዌሩ ላይ ፋይሎችን በመምረጥ ሪስቶር ወይም ወደ ኮምፒውተሩ ዶክመንት ማስቀመጫ ሴቭ ያድርጉት። 👉 ከዛም ሚሞሪውን ፎርማት አድርገው እዛው ኮምፒውተር ላይ አንድ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ሚሞሪው ፋይል እንደሚቀበል እንደሚይዝ ማረጋገጥ። የማይዝ ከሆነ ተበላሽቷልና። ከእንግዲህ አይሰራም። ፎርማት ሲያደርጉት ፎርማት ያደረገ መስሎ ነገርግን እዛው መልሶ ራሱ የነበርውን ከሆነም ሚሞሪው ተበላሽቷል ድጋሚ አይሰራም። ሌላ አዲስ ገዝተው መጠቀም ነው። አዲስ ሲገዙ ኦርጂናል መሆኑን በደንብ ያረጋግጡ። 👉 ስካን ሲያደርጉ ፋይሉን የማይመልስ ወይም የማያሳይ ከሆነ ብዙ አይልፉ ሚሞሪ ኮረፕት አድርጎ ሙሉ በሙሉ ተበላችቷል ማለት ነው። 📌 ብዙ ጊዜ ሚሞሪ ኮረፕት ሚያደርገው በቫይረስ እና በተለይ እየሞላ ክፍት ቦታ አንሶ ካሜራ ከፍተን ስንቀርጽ ፣ በተደጋጋሚ ፍሪ ስፔስ እያለ ሏን ዝም ስንል.. ወዘተ ነው።
Jul 03, 2024