ሰላም....ቢቻላችሁ እርዳታችሁ በጣም ያስፈልገኛል። የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ ወደ 10 ወይም 11 ዓመት ገደማ በጓደኝነት የማውቃት ልጅ አለች። ከ 5ኛ ክፍል ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ አብረን ነው ምንማረው አብረን ነው ምንውለው ምን አለፋቹ ለአዳር ብቻ ነው የምንለያየው። ታድያ ይህች ልጅ ከሆነ ጊዜ በኋላ ስሜቷ አየተቀየረ ወደፍቅርመጣ አኔም እንደዛው። አሷ ያደገችው አያቷ ጋር ነው እናቷ ውጪ ናት አባቷ ደግሞ ሌላ ትዳር አለው። እና እኔ ማረግላት እንክብካቤ ካቅሟ በላይ ሆኖባት ከአባቷ አብልጣ እስከማየት ደርሳለች። አኔ በበኩሌ አብሬያት በኖርና ፈጣሪ ፈቅዶ ወደ ትዳርም ብንደርስና ልጆች ቢኖሩን ምኞቴ ነው። ግን ፈተናው እሷ እና አብዛኛው ቤተሰቧ ፕሮቴስታንት ናቸው አኔ ደግሞ ኦርቶዶክስ። ችግሩ ግን እሱ አደለም ስሐ ሃይማኖት በደምብ ነው ምናወራው እኔም ቤ/ክ አገልጋይ ስለሆንኩ ማቀውን አካፍላታለሁ እሷም ወደ ኦርቶዶክስ ለመምታት አዝማምያ ላይ ናት። እዚጋር ነው ፍርሀቴ እኔ ከቤተሰቦቿ እና አሳዳጊዎቿ ለይቼ ምትፈልገውን ህይወት ባልሰጣትስ? እና ደግሞ በእድሜም እኩዮች ነን እሱስ ችግር አያመጣብንም ወይ?? የሚል ነው ጥያቄዬ
Jul 02, 2024ጨዋ የጨዋ ልጅ ያሰብከውን ያሳካልህ ወንድሜ 😍🙏🙏🙏
Jul 03, 2024