Do you believe slavery should existed at this time and age or you disagree with this imam
ከመጽሀፍ ቅዱስ አስገራሚ ይዘቶች መካከል (የሕያ ኢብኑ ኑህ) በዚህ ክፍል የምንመለከታቸው አንቀፆች ብዙውን ጊዜ ስናነባቸው ፈገግ የሚያደርጉን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ አሳዛኝ የሆኑ አልፎም አስደንጋጭ የሆኑ የባይብል አንቀፆችን ነው፡፡ እነዚህ አንቀፆች ቅዱስ በተሰኘ መጽሀፍ ውስጥ ሊኖሩ የማይገቡና ፈጽሞ የመለኮታዊ ቃልነትን ካባ ያልተላበሱ ናቸው። 1. ታላቁ ገዳይ እንደ መጽሀፍ ቅዱስ መሠረት አምላክ በሆነ ወቅት ደስ ካላለው "ለምን ይሄን አያችሁ?" ብሎ ሳይቀር ህዝብ በመደዳ ጨፍጭፎ ሊያስለቅስ ይችላል፡፡ " ወደ እግዚአብሔርም ታቦት ውስጥ ተመልክተዋልና የቤትሳሚስን ሰዎች መታ፤ በሕዝቡም ከአምስት ሺህ ሰው ሰባ ሰዎችን መታ፤ እግዚአብሔርም ሕዝቡን በታላቅ ግዳይ ስለ መታ ሕዝቡ አለቀሰ።" (መጽሐፈ ሳሙኤል ቀዳማዊ 6:19) የሚገርመው የእንግሊዝኛው ንጉስ ጀምስ ቅጅ የሚለው Fifty thousand (አምሳ ሺህ) ሲሆን ወደ አማርኛ ሲተረጎም ግን አምስት ሺህ ሁኗል፤ የቱ ነው ትክክል? ለማመሳከር እንዲያግዝ የእንግሊዝኛውን አንቀጽ ከታች አስቀምጣለሁ፡፡ "And he smote the men of Beth-shemesh, because they had looked into the ark of the LORD, even he smote of the people fifty thousand and threescore and ten men: and the people lamented, because the LORD had smitten [many] of the people with a great slaughter." (1Samuel 6:19)
Jul 01, 2024