ስለ ሥላሴ አስር ክርስቲያኖችን ብንጠይቅ አስሩም በስላሴ ላይ የተለያየ አመለካከት እና እምነት ነው ያላቸው የክርስቲያኖች ፈጣሪ ለምንድነው አማኙን በዚህ ልክ ማወዛገብ የፈለገው?
Jul 01, 2024የተለያየ አመለካከት እና እምነት ነው ያላቸው??? በቅድስት ስላሴ አንድነት እና ሶስትነት 10ሩንም ብትጠይቅ የተለያየ አረዳድ ሊኖራቸው ይችላል እንጂ እምነታቸውም አመለካከታቸውም አንድ ነው። እርሱም አምላካችን አንድም ሶስትም ነው ስሙም እግዚአብሔር ነው። እንዴት አንድም ሶስትም ይሆናል ብለህ ስትጠይቃቸው ነው እንደተረዱት ሲያስረዱህ ልዩነት ሊመጣ የሚችለው። ለዛ ደሞ ትክክለኛውን መልስ ለማግኘት ከፈለክ መፅሀፍትን ማንበብ እና መንፈሳዊ ኮሎጅ ውስጥ ምናምን መማር ነው።
Jul 01, 2024