Hey guys Please be lela melku atwsedubng gn just question nw ... muslim gn indet nw mtamnut malete allah man yihun mn yihun ataqum beza lay quran ke semay nw yewerdw tlalachu tetsfo nw yewerdw ?!?) Mayamnutn be megdel nw mtsmamut quran lay bzu mayasamn neegeroch alu chirash beqa bezalay allah areb nw inde 🤔 cuz be amarnga rasu azan mnamn yelm weys mndnw gudu how u believe that (memert mnamn ayseram eziga) please meches mkniyat yikoral🙂
Jun 30, 2024"በሌላ መልኩ አትውሰዱብኝ" ስትል ለመተቸት ፈልጌ አይደለም ለማለት የፈለግክ ይመስለኛል። እንደዛ ከሆነ ጥያቄ ስትጠይቅ ሙስሊም ካልሆኑ አካላት የሰማከውን ወይንም ተቆርጦ የመጣ ኢስላማዊ ንግግርን ይዘህና በዛ ነገር ኢስላምን እየፈረጅክ አትጠይቅ። የልቁንስ የያዝከውን ነገር እንደዚህ ነው አንዴ ብለህ አስቀድመህ ጠይቅ። ከዚያ ለምን እንደዚህ ሆነ ብለህ ጠይቅ። በመጀመሪያ የአላህን ምንነት አያቁም ያለህ ተሳስቷል። አላህ አለማቱን የፈጠረው ብቸኛው እና ሀያሉ አምላክ ነው። ስሞቹ አና ባህሪያቶቹ ላይ ብንለያይም በማንነቱ ላይ አንድነን። ይህን ለማረጋገጥ የአረበኛ ብሉይ ኪዳን ላይ አላህ የሚለውን ስም ፈልግ። አላህ የሚለው ስም እና እግዚአብሔር የሚለው ስም በመለያየታቸው ግራገብቶህ ከሆነ:- አላህ ማለት ትርጉሙ ኡሉሂያ ከሚለው ቃል የተመዘዘ ሲሆነ ኡሉሂያ ማለትም ደግም አምልኮት የሚል ፍቺ ይኖረዋል። አላህ ማለት ደግም አምልኮት የሚገባው ብቸኛ አምላክ ማለት ነው። እግዚአብሔር ማለት ደግሞ የብሄር ገዢ ወይንም ባለቤት የሚለውን ትርጉም ያሳያል።ይህንን ስም ደግሞ እኛ ሙስሊሞች እንደ ጉድለት ሰለምናየው አንቀበለውም። ቁርአን ከሰማይ የወረደው በጅብሪል/ገብርኤል አማካኝነት ሲሆን ጅብሪልም ለነብዩ ሙሀመድ (ሰላት እና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) በየጊዜው እየመጣ ያስተምራቸው ነበር እሳቸውም የተማሩትን ለሰሀቦች/ባለደረቦቻቸው ያፅፉ ነበረ። ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችን በጭፈን በመግደል አናምንም። ባይሆን ሀይማኖታችሁን ቀይሩ ብሎ ሊገለን የመጣን በመግደል እናምናለን። ላያሳምኑህ የቻሉ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ። የነገሮቹን አሳማኝነት ከማሰብክ በፊት የመፅሀፉን አሳማኝነት ማሰብ አለብክ። ምክኒያቱም ይህ ሁሉን አዋቂ የሆነው ፈጣሪ ንግግር መሆኑን ካወቅክ በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ያገኘከውን እውቀት ይዘህ የፈጣሪን ንግግር ትክክል አይደለም ማለት አትችለም። ብዙ ማያሳምኑ ነገሮች አሉ ላልከው አንድ በአንድ ከነገርከኝና ጊዜ ካለክ በአላህ ፍቃድ ልመለስለህ እችላለው። አላህ አረብ ነው እንዴ ከማለትከ በፊት ማሰብ ያለብክ ነገር አለ። እሱም አረብ ማለት አረብ ከሚባል የሰው ስም የተመዘዘ የብሄር ወይንም የጎሳ ስም ነው። ይህ ማለት ደግም አረቦች አረብ ከሚባለው ሰው ጋር ዝምድና አላቸው ወይንም የለጅልጆቹ ናቸው ማለት ነው። አላህ ዘር አንዲኖረው የግድ መውለድና መወለድ አለበት። አላህ ግን ጥራት ይገባው የሚወልድ የሚወለድ አይደለም (ባህሪው አይደለም)። አረበኛ ላልከው አሁንም የምደግምልክ ኢስላም ትክክለኛው ሀይማኖት ነው ብለክ ከተቀበልክ የአላህ(አለማቱን የፈጠረው ጥበበኛ አምላክ) ጥበብ በኛ እውቀት መዝነክ ትክክል አላደረገም ማለት አትችልም።ይህ ማለት ግን ይህን ያደረገበት ምክንያቶች ምንም አናውቅም ማለት አይደለም። ለምሳሌ አንተ እንዳነሳከው አላህ የሚለው ስም አወዛግቦክ ነበረ። እኛ በአረበኛ የመጣውን ነገር ሁሉ ቶርጉመን ቢሆን በፈጣሪያችን ስም እንኳን እንደ ክርስቲያኖች በተቃረንን ነበረ። ማለትም ካስተዋልከው ኢትዮጵያ ውስጥ እግዘብሔር አረብ ሀገር ኢላህ በኢንጊልዘኛው ጋድ ወዘተ ተብሎ በመጠራቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ የግብፅ ኦርቶዶክስ የሩስያ ኦርቶዶክስ ወዘተ በማስባል በክርስቲያኖች መሀል ክፈተት ፈጥሯል። ከእነደዚህ አይነቱነ ልዩነት ሁሉንም ነገሮች በትርጉማቸው አለመጠቀማችን ጠቅሞናል። በመምረጥ አንተ ላታምን ትችላለህ ነገርግን መፅሀፍ ቅዱስም በአማረኛ ወይንም በግዕፅኛ አሎረደም። ይህ ማለት ደግሞ ኢሰላም ብቻ አይደለም አንድን ቋንቋ በመምረጥ የፈጣሪ ንግግር እንደወረደ የሚያስተምረው ማለት ነው። አላህ ቁርእንን በአረበኛ ከማውረዱ በፊት ተውራትን/ቶራን በኢብራይጥስ አና ኢንጂልን/ወንጌልን በሶርያኛ አውርዶ ነበረ።
Jun 30, 2024