ሰላም ቤተሰቦች እቺን ጥያቄ እንዳታልፋዋት የናንተ ሃሳብ በጣም ነው ሚያስፈልገኝ በጣም የምወዳት ልጅ አለች ከቁመቱዋ ውጪ😁 ቆንጅዬ ነች ከተዋወቅን ከ 3 አመት በላይ ይሆነናል ግን እንደምወዳት እስካሁን አልነገርኩዋትም ምክንያቱም እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም ፍላጎቱዋ ምን እንደሆነ....እና ያገቡ ልጆች ያላቸው የወንድ ጉዋደኛ አሉዋት ብዙ ጊዜ ከነሱ ጋር ነው ምታሳልፈው ጊዜዋንም ለነሱ ነው ምትሰጠው በዚህ የተነሳ ብዙ ሰው ልክ እንዳልሆነች ይነግሩዋታል እሱዋ ግን ምትሰማ ነገር አይደለችም ከኔ ጋር ብዙ ጊዜ በ አካል ስለማገኛት እናወራለን ምንም ምትደብቀኝ ነገር የለም ግን ምንም ነገር ብትፈልግ የፈለገችው ነገር እኔጋር ቢኖር እንኩዋን እኔ ጋር ከመደወል ሌላ የማታውቀው ሰው ጋር ብትደውል ይቀላታል እና ብዙ ወንዶች ለትዳር እንደሚፈልጉዋት ትነግረኛለች ግን ደግሞ ሳላገባ እድሚዬ ሄደ ትለኛለች ሳስበው ለኔ ቦታ እና ጊዜ መስጠት አትፈልግም ለ ጉዋደዬቼ እንደምወዳት ስነግራቸው እሱዋ ላንተ አትሆንም ነው ሚሉኝ :: እንደምወዳት በብዙ ነገር ለሳያት ሞክሬያለሁ እሱዋ ግን ፍላጎት ያላት አይመስለኝም የሆነ አለ አይደል የጥቅም ሰው ነች እና ልርቃት እና ቢቀርብኝ ይሻላል ብዬ እያሰብኩ ነው ምን ትመክሩኛላችሁ?
Jun 29, 2024ምን ጥያቄ ያስፈልገዋል ይሄ Forget her dude
Jun 29, 2024