For Orthodox brothers & sisters እመቤታችን ድንግል ማሪያም በ21 በ03 እና በ16 ለምን የተለያየ ስም እና ቀን ተሰጣት እናደግሞ በ16 እና በ03 ስራ እየሰሩ በ21 ስራ የማይሰሩ ሰዎች አሉ የሚያከብሩ እሄ ትክክል ነዉ ትላላችሁ ካልሆነስ እምነታችን በልማድ ተመስርተን እንጂ ገብቶን አይደለም ማለት ነው ? በቅንነት መልሱልኝ
Jun 28, 2024በ1 ልደቷ በ3 በዓታ = ቤተ መቅደስ የመግባቷ በ16 ኪዳነምሕረት = ወካዕበ ተማኅፀነ በማርያም እምከ እንተ ይእቲ እግዝእትነ ወትምክሕተ ዘመድነ በወሊዶተ ዚአከ እስመ አንተ ትቤላ ዘገብረ ተዝካሪኪ ወዘጸውዐ ስመኪ ሕይወተ ዘለዓለም የሐዩ (ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፣ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርይያችን መመኪያ ናት፣ አንተ መታሰቢያሽን ያደረገ፣ ስምሽንም የጠራ የዘለዓለም ደኅንነትን ይድናል ብለሃታልና » በ21 ዕረፍቷ ነውና ። እንዲኹ በሌሎች ቀናቶችም አሉ ። በ21 ሥራ የማይሠሩት ትክክል ናቸው ይኽም ግዝት በዓል ነውና ። (ሥራ የሚሠራ ኹሉ ግዝት ውስጥ ነው ) ሌላው እመቤታችን 33 በዓላት አሏት ቢቻል 33ቱን ካልተቻለ አምስቱን ማክበር የክርስቲያን ኹሉ ግዴታ ነው ።
Jun 28, 2024