ጨጓራዬን ያመኛል ማለት ምግብ ስመገብ ወዲያው የመጥገብ ስሜት ይሰማኛል ከበላሁም በኃላ ጉሮሮዬ ጋር ያንቀኛል አልትራሳውንድ ተነስቼ ኖርማል ነው ተብዬ ነበር አሁን ግን ክብደት በጣም በጣም እየቀነስኩኝ ነው ...እንደዚህ አጋጥሞት የሚያውቅ አለ? የጨጓራ በሽታስ የክብደት መቀነስ ያስከስታል?
Jun 21, 2024እኔ ጨጓራ በጣም እታመም ነበር! ምግብ መምረጥ አስጀመረኝ፣ ውሃ እንኳ ስጠጣ የሚያብስብኝ ጊዜ አለ ከተነሳብኝ። በዛ ላይ የሚያመኝም 2 ዓይነት ነው። አንዱ የጨጓራ ባክቴሪያ የሚሉት የጨጓራ አሲድ እየረጨ መሃል ላይ የሚበላ እየሰፋም ሆድ የሚያቃጥል ሲሆን አንዳዴ ቀጥታ የበላሁት ምግብ በተለይ በባዶ ሆድ የምበላው ምግብ ካልተስማማው እያነቀ ይይዘኝ ይጀምርና ጎንበስ እስከማለት፣ የመራመድ እንቅስቃሴም የሚጠላ ወግቶ የሚዝ ነው። ይኼኛው ያ የበላሁት ምግብ እስካልወጣ ድረስ ሌሊቱን ሁሉ የሚያስጨንቅ ነው። ሆድ የመንፋት፣ ቦርጭ እስኪመስል ድረስ ብዙ ብዙ አየንት አስቸጋሪ ለሚያይክ ሰው ጤነኛ ምትመስል ክፉ በሽታ ነው። ከዚህ ለመፈወስ ምንም ዓይነት ህክምና አያድነውም። በፊት ስፔሻሊት ድረስ ሄጄ በምግብ ራስህን ጠብቅ የሚስማማህን ለይ ነው የተባልኩት። ይኼም ትትክክል ነው። አንዱ ምስር በርበሬ ሚጥሚጣ ሲል ሌላው ደሞ አልጫ ነገር የማይስማማው አለ። አንዱ ወተት ሲያረጋጋው አንዱ ጭራሽ ያብስበታል። መፍትሔ ያገኘሁት የዳንኩት በጸበል ነው። የአቡነ እጨጌ ዮሐንስ ጸበል ሰው አምጥቶልኝ ተስዬ በተኛሁበት ጠጥቼ ነው። ከዳንኩም በኋላ ገዳሙ ድረስ ሄጄ መስክሬ ነው።
Jun 21, 2024