ሰላም እንዴት ናችሁ ምን መሰላችሁ ለምን እንደሆነ ባላውቅም በትንሽ ነገር በጣም እናደዳለሁ ከፍቅረኛዬ ጋር በጣም ነው የምንዋደደው ብዙ ጊዜ አብረን ቆይተናል ምንም አይነት ነገር በመሀላችን አልጎደለም ከምታስቡት በላይ እንዋደዳለን በጣም ግልፅ ነን እንደ ጓደኛ እንደ እህት ወንድም እንደፍቅረኛ በቃ እንደሁሉ ነገር ነው የምንተሳሰበው ግን እኔ ትግስት የለኝም በጭራሽ በትናንሽ ነገር ራሱ እስክታመም ደም ግፊቴ ጨምሮ ሰውነቴ አልታዘዝ እስኪለኝ ነው እልህ ውስጥ የምገባው የምናደደው በዚህ ምክንያት እሷንም ማይሆኑ ቃላት አንዳንዴ እናገራታለሁ ከመጠን በላይ ስናደድ ራሴን በጣም ከሚባለው በላይ ለመቆጣጠር እሞክራለሁ ግን አልቻልኩም ከተናገርኳትም ቦሀላ መልሶ ይፀፅተኛል ያረገችኝም ነገር ያናደኛል የተናገርኳትም ነገር ይፀፅተኛል በ 2 ነገር ህሊናዬ ይቀጣኛል ግን አንዳንዴ ይቅርታ ለመጠየቅ ራሱ ሞራሉ ማይኖረኝ ነገር እናገራታለሁ ከዛ ይቅርታ ብላት ነገስ ራሴን መቆጣጠር አቅቶኝ እንደማልደግመው በምን አውቃለሁ ብዬ ይደክመኛል በቃ የምጠላው ባህሪዬ ነው እንዴት አርጌ ስሜቴን ልቆጣጠር እንዴት በትንሽ ነገር ንዴት እና እልሄን ላስወግድ ከምታስቡት በላይ እየጎዳኝ ነው በቃ ይሄ ነው ችግሬ እንጂ ከዚ ውጪ እንደኛ ሚዋደድ እና ሚተሳሰብ እንደኛ ግልፅ ሰው ያለም አይመስለኝም አመታትንም አስቆጥረናል።
Jun 20, 2024ያልከው ነገር ከባድ ቢሆንም ወደፊት ነርቭን ጨምሮ ብዙ በሽታዎችን ሊያመጣብክ ይችላል መፍትሄው በጣም ከሚያናድድክ ሰው ጋር ዋል ቲኒሽ ስትቆይ እየለመድከው ትመጣለህ እራስህን መቆጣጠርም ትማርበታለክ ብዬ አስባለው የኔ ሐሳብ ነው
Jun 21, 2024