አንድ ጓደኛችን ነበረች ታማ በቅርቡ ልንጠይቃት ሄድን ቤት ውስጥ ሰዉ ሲገባ ብቻዋን አይተዋትም መጥተው ይቀመጣሉ በስርአት እያወራች ይስቁባታል ማይረባ ነገር እንደሆነ አይነት እንጀራ አባቷ እንደማይመቻት እናቷ ስትኖርና ሳትኖር እኩል አደለም ትለን ነበር አሁን ሳስበው ፆታዊ ጥቃት እንዳደረሰባት ይሰማኛል ታላቋን ሞክሮ ነገር በጣም ተጣልታው ወደሷ ዞሮ አይነት እኛ እንድናገኛት አይፈልጉም ሳይካትሪስት ጋር ጀምራ ነበር አቋርጠውባት ሌላ ሃኪም ቤት ለወራት ተኝታ መጥታ "እብድ ብቻ ነው ያለው ቤተሰብ ይናፍቀኛል ፀጉሬን ላጩኝ መርፌ ይወጉኛል የስነ ልቦና ባለሙያ ጋር ነው መሄድ ምፈልገው ግን እምቢ አሉኝ ደግመዉ እዛ ሊወስዱኝ ነው እናቴ ምንም አትሰማኝም ሌላ ሰዉ ሆናብኛለች " አለችን ምንም መንገር አትፈልግም እምነት አጥታለች ቤት አትሆንም ብቻዋን ታወራለች እናቷ ከኔ ጋር ነው መሆን ያለብሽ ትምርት ምንም አያረልሽም የትም አትደርሺም ለሁሉም ረፍዶብሻል እያለች ጭንቅላቷን ትሞላታለች እህቷ በጣም ራስ ወዳድ ናት እንድትቀርባት አትፈልግም። ቤተሰቦቿ ሳያቁ ማሳከም ምንችልበት ሁኔታ ካለ በተለይ ነፃ ምክንያቱም ተማሪዎች ነን ቤተሰቦቿ ቢያቁ ድጋሚ ይወስዷታል ወይ ጭራሹን ሰው እንዳታገኝ ያደርጋሉ እባካችሁን የምታቁት ቦታ ወይም ሰው ካለ እና እምነቷ እንዲመለስ ጭንቀቷ እንዲቀንስላት ጥሩ እንድታስብ ተስፋ እንዲኖራት ማድረግ የምንችለውን ጠቁሙን
Jun 13, 2024ፀበል ውሰዷት
Jun 13, 2024