If you're not Muslim scroll, so I'm Muslim girl n በትክክለኛው እምነት ላይ በመፈጠሬ እና ከቤተሰቦቼ ስለወረስኩት ሳይሆን ትክክለኛነቱን አንብቤ የመረዳት አክሰሱም ስለነበረኝ ደስተኛ ነኝ፣ ግን ሁሌ ጥያቄ የሚሆንብኝ ነገር የነብዩ ሙሀመድ(peace be upon him) አኢሻን(ረ.ዓ) በዛ እድሜዋ ማግባታቸው ነው፣ የባህል ተፅዕኖ ነው ወይስ ዛሬም ቢሆን ማድረጉ እንደ ሱና ይታያል? ከላይ እንዳልኩት non muslimochን አይመለከትም::
Jun 07, 2024.............ሙስሊም ወገኖች መሀመድ አይሻን በስድስት አመቷ አግብቶ በዘጠኝ አመቷ ግንኙነት እንደፈጸመባት የሚናገሩትን ምንጮቻቸውን ለማስተባበል ወይም ሌላ ትርጉም ለመስጠት ሲሉ እስልምና ህጻናትን ማግባት ቢፈቅድም የህጻናት ግንኙነትን እንደማይፈቅድና ለግንኙነት አቅም ለመድረስ የግድ ሴቷ ጉርምስና መድረስ እንዳለባት ሲናገሩ መስማት የተለመደ ነው።(መሀመድም ከአይሻ ጋር የተኛው ከጎረመሰች በኋላ ነው ይላሉ) ምንጮቻቸው ግን ይሄንን አቋም አይደግፉም። ከቁርዓን ስንነሳ ቁርአን (65:4) ላይ ወንድ ሙስሊሞች ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ሲፈልጉ ሚስቶቻቸው ገና አደፍ (የወር አበባ) ያላዩ ከሆኑ እርጉዝ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ሶስት ወር መጠበቅ እንዳለባቸው ይናገራል።ታዲያ መጀመሪያውኑ የወር አበባ ያላዩ ሴቶች ላይ ግንኙነት መፈጸም ካልተቻለ ለምን እነዚህ ህጻናት እርግዝናን ለማረጋገጥ ለወራት መጠበቅ አስፈለጋቸው ብለን መጠየቅ አለብን። ኢብን አባስ በተፍሲሩ ላይ ሲጽፍ አንድ ሰው መሀመድን ቀርቦ "በጣም ህጻን ስለሆኑ የወር አበባ የማያዩት ሴቶች ኢዳ መጠበቅ አለባቸው?" ብሎ እንደጠየቀውና መሀመድም ሶስት ወር መጠበቅ እንዳለባቸው እንደነገረው ይዘግባል።...[1] ኢብን ከሲርም በተመሳሳይ እነዚህ ህጻናት ባላቸውን ከመፍታታቸው በፊት አርግዘው ሊሆን ስለሚችል ሶስት ወር መጠበቅ እንዳለባቸው ይናገራል።...[2] አስተውሉ እያወራን ያለነው ጉርምስና ስላልደረሱ/የወር አበባ ስላላዩ ሴቶች ነው። እስልምና የህጻናት ጾታዊ ግንኙነትን የሚከለክል ከሆነ መሀመድ እዚህጋር ነበር "እንዴት ህጻናት ኢዳህ ይጠብቁ ትላለህ? በእስልምና የህጻናት ግንኙነት ሀራም መሆኑን አታውቅምን? ኢስተግፊሩላህ!" ማለት የነበረበት። ታዲያ ጉዳዩ በዚህ አያበቃም ኢማሙ አልሚስሪም በሸሪአ ትንታኔ መጽሀፉ ላይ "ጉርምስና ያልደረሰች ሴት ባሏን ስትፈታ ለሶስት ወር ኢዳህ መጠበቅ አለባት" ብሎ ቀጥታ ያስቀምጠዋል።...[3] ይሄንን ጠንቅቀው የሚያውቁት ሙስሊም አቃቤ እምነቶች አስቂኝም አሳዛኝም ማብራሪያ ሲያስቀምጡ ታይቷል።መሀመድ ሂጃብ አንድ ጊዜ መንገድ ላይ ባደረገው ንግግር "ከስድስት ወይም አምስት አመት ህጻናት ጋር ግንኙነት የማንፈጽመው ለጉርምስና ስላልደረሱ ሳይሆን አካላዊና ስነልቦናዊ ጉዳት ሊያመጣ ስለሚችል ነው" ብሎ ተናግሯል።...[4] ስለዚህ በመሀመድ ሂጃብ መሰረት አንዲት ህጻን ግንኙነት መፈጸም አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ ጉዳት ካላመጣባት ጉርምስና ላይ ባትደርስም በአምስትም በስድስትም አመት ግንኙነት መፈጸም ትችላለች ማለት ነው። ይህ የዞረበት አስተሳሰብ ምን ያህል አሳማኝ ነው? የስድስት አመት ህጻን ግንኙነት አድርጋ አካላዊ ጉዳት አይደርስባትም ይባላልን? እንደ አይሻ ያሉ ግንኙነት ሲፈጽሙ ገና አሻንጉሊት ያልጣሉ (ሱናን አኒሳዕ 3378) ህጻናትስ እንዴት ምንም ጉዳት አይደርስባቸውም ይባላል? የዚህ አመለካከት ሌላኛውና ዋነኛው ችግር ለግል ትርጓሜ የተጋለጠ መሆኑ ነው። ህጻናት መቼ ግንኙነት እንደሚፈጽሙ የሚወሰነው "ጉዳት ይደርስባቸዋል ወይስ አይደርስባቸውም?" በሚለው ሀሳብ ላይ ከሆነ ይሄንን ደረጃ የሚቆጣጠርና የሚያስጠብቅ አካል ያስፈልጋል። ሙስሊም ወንዶች መቼም ዶክተር አይደሉምና ህጻን ሚስቶቻቸው መቼ ለግንኙነት ብቁ እንደሚሆኑ ማወቅ ስለማይችሉ በአንዱ ቀን ተነስተው ግንኙነት መፈጸማቸው አይቀሬ ነው። ይህ ደግሞ ልጅቷን ለአካላዊም ለስነልቦናዊም ጉዳት የሚያጋልጥ ከመሆኑ ባለፈ ለሰዎች የግል ትርጓሜ የተጋለጠ ስለሆነ ውጤታማ ሂደት ሊሆን አይችልም። የአለም ጤና ድርጅት "በህጻናት ላይ የሚፈጸም ጾታዊ ግንኙነት ሀይለኛ የአዕምሮ ቀውስ የሚያስከትል ብቻ አይደለም። ብዙ የሳይንስና የቤተሙከራ ግኝቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ይህ ተግባር የወረደ የራስ መተማመንን ፣ ስሜትን መቆጣጠር አለመቻልን ፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር መቀራረብ አለመቻልን እና ዘላቂ የስነጾታ ችግሮችን ጨምሮ ብዙ የስነልቦና ጉዳት ያመጣል" ይላል።...[5] እንግዲህ ሙስሊም ወገኖቻችን እስልምና ህጻናትን አስገድዶ የመድፈር ፍቃድ እንደሰጠ ለማስተባበል ሁለት አማራጭ አላቸው።የመጀመሪያው ከላይ ያየናቸውን ምንጮች ክዶ እስልምና የህጻናት ግንኙነትን አይፈቅድም ማለት ሲሆን ሁለተኛው አማራጭ ደግሞ የአምስትና የስድስት አመት ህጻናት በራሳቸው ፍቃድ ጾታዊ ግንኙነት መፈጸም ይችላሉ ብሎ መናገር ነው። [1] Ibn Abbas , quran tafsir , page 776. [2] Ibn kathir , quran tafsir (65:4) [3] Ahmed ibn Naqib al-misri , Reliance of the traveller , page 569. [4] https://youtu.be/sCFeQpZEWeg [5] WHO , Comparative quantification of health risks , child sexual abuse , page 1853. © @Jacobite_apologetics27
Jun 08, 2024