ሰላም እህት ወንድሞቼ አንድ ነገር በሉኝ እስቲ...Remedial ፈተና ደረሰ እና ከጊቢ ከ30% ዝቅተኛዬ 23 ነው አሪፍ ሰርቻለው ብዬ አስባለው አጠናለውም ዋናው ፈተና ሲቃረብ ግን ምን እንደሆንኩ እንጃ ፈራሁ ጭራሽ ለጊቢ ፈተና የተዘጋጀሁትም እየረሳሁት ነው አሁን ጥያቄ መስራት ሲገባኝ በድጋሚ ሙሉ unit ለማየት እየተገደድኩ ነው እና ማስታወስ አለመቻሌ በራሱ እያበሳጨኝ ሌላ ታሪክ ውስጥ ነኝ ማሰብም አቁሚያለው በቃ ተኝቼ ነው ምውለው ሀይለኛ ጭንቀት ውስጥ ገብቻለው ምን ማድረግ ነው ያለብኝ? ባለፈው አመት የተፈተናቹ እንዴት ነው ያለፋቹት? ኦንላይን መሆኑ ደሞ 🥹እስቲ አማክሩኝ በወላዲቷ🤲
Jun 07, 2024ዝቅተኛዬ 23 እና ቆንጆ እኮ ነው።አንቺማ ዘና ብለሽ ነው የምታልፊው የምር።እኔ የአምና ሪሜዲያል ሰነፍ ነበርኩ አለኩ ግን ተንጠልጥዬ አልፌ አለሁ ያው የclassu በደንብ ያገዘኝ ቢሆንም።በቃ አትጨነቂ ባታጠኝም ትሰሪዋለሽ ታልፊያለሽ።ምርጥ ሰርተሻላ የclassun ስለዚ አትጨነቂ ፈታ በይልኝ እወድሻለሁ 😘😘
Jun 07, 2024