Betam becheginet eyetesemagi nw raseshin atefi atfi nw yemilegi mn laderegi hiwot merogal
Jun 06, 2024እራስሽን እንዳታጠፊ ምንም ድርጊት ውስጥ እንዳትገቢ እንጂ ስሜቱ ትክክለኛ ነው. . . ሁሉም ሰው በሚባል ደረጃ በዚህ ስሜት ውስጥ ያልፋል ነፍስሽ እስከ ሞት ድረስ ታዝናለች፤ የሲኦልን ጠርዝ ነክተሽ ትመለሺያለሽ አይቆይም ከዚህ ስሜት ውስጥ ትወጪያለሽ እመኚኝ. . . ጥቂት ሰው ከዚህ ስሜት ውስጥ የሆነ ትርጉም ይዞ ይወጣል ነፍስሽ ጠንካራ የምትሆንበት መንገድ ይሄ ስለ ሆነ ነው. . . ማድረግ ያለብሽ ነገር ሰውነትሽን ልቀቂው የአእምሮሽን ጭቅጭቅ አታዳምጪው. . . ጸሎት የማድረግ አቅም ካለሽ ጸሎት አድርጊ ብቸኛ ነኝ ብለሻል ወክ ውጪ ረጅም መንገድ ዝም ብለሽ ሂጂ. . . Exercise ለመስራት ሞክሪ. . . የሆነ ማስታወሻ ደብተር አዘጋጅተሽ የተሰማሽን አንድም ሳታስቀሪ ጻፊበት. . . ማልቀስ ካለብሽ እስኪወጣልሽ አልቅሺ ብቻ ሰውነትሽን ልቀቂው ተንፈስ ይበል ከዛ የራስ ማጥፋት ስሜቱም ድምጹም ይቀንሳል. . .
Jun 06, 2024