አንድ ጤያቄ ለሙስሊሞች እኔ ኦርቶዶክስ ነኝ እና ሙስሊሞች ስሂር ማድረግ ከሀይማኖታቹ ዉጪ ላለ ሰው ይፈቀድላችኋል አቃለሁ ስሂር ሽርክ ነው ምናምን እነደምትሉ ግን እኔ በሂወቴ ስላጋጠመኝ ነው አብሮ አደግ ዘመዴ በሏቸው አክራሪ ሱኒ ሙስሊሞች አሁን በቅርብ ስሂር እንዳደረጉብኝ አወኩ እነሱ ብቻ አደለም የነሱ ሌላ ሙስሊም የቆየች ጓደኛቸው እና አብሮኝ አንድ ጊቢ ዩንቨርስቲ የተማረ ልጅ ጂኒ ለፍልፎ ምናምን አደለም ያወቅት በአይኔ በብረቱ ነው ያየኋቸው ማርያምን እና ወይ ለካፊር ስሂር ይፈቀዳል ወይ ለሀይማኖታችሁ ትዋሻላለቹ በቅንነት ሳትሳደቡ መልሱ ሀይለኛ depression ዉስጥ ነው ያለሁት በዚ ምክንያት እንደዚ አይነት የደረሰባችሁም ካለ ክርስቲያኖች ብታስረዱኝ
May 29, 2024አጠያየቅህ የውሸትና ለዛ ቢስ መሆኑን ለማወቅ ጥያቄህን ስትጀምረው "አንድ ጥያቄ ለሙስሊሞች" ብለህ ጀመርክና መጨረሻ ላይ ጥያቄህን "ክርስቲያኖች ብታስረዱኝ" ብለህ 180° ተቀለበስክ። ከሀይማኖታችን ውጭ ድግምት እንደሚፈቀድልን #ከቁርአን ወይም #ከሐዲስ አንዲትን አንቀጽ ከጠቀስክልኝ 20,000 ብር በአካውንትህ ልላክልህ! በጣም ካረጋገጥክልኝ 50,000 ብር አደርግልሃለሁ። አንተ ኢስላም በድግምት እና ደጋሚ ላይ የሚወስደውን እርምጃ ብታውቅ ኖሮ ሙስሊም ድግምት ሲሰራ ብታይ እንኳ "እምነታችሁ በድግምት የሚወደስደውን እርምጃ እያወቅክ እንዴት እንዲህ ታደርጋለህ?" ብለህ ትጠይቃለህ! አነጋገርህ ያለ እውቀት የተተፋ ንግግር እንደሆነ ጥርጥር የለውም። ስለኢስላም የማያውቁትንም ለማምታታት የተጻፈ ቅጥፈት መሆኑን ለማወቅም ከባድ እውቀት አይፈልግም። አይደለም ድግምት መስራት ሊፈቀድልን ቀርቶ ጠንቋይ ቤት ሄደን ጠንቋዩ የተናገረውን ቃል "እውነት ነው" ያልን እንደሆነ አላህ የ40 ቀን ስግደታችንን አይቀበለውም። ሙስሊም ነኝ ባይ ደጋሚ ከሆነማ በሰይፍ ነው ጭንቅላቱን ከአንገቱ የሚለይለት! በመሠረቱ ጥንቆላ ለሰይጣን መገዛትን ስለሚያስገድድ አንድ ሙስሊም ጠንቋይ ቢሆን ወይም ጠንቋይ ጋር ሄዶ ቢያስጠነቁል በአላህ ላይ ሌላን አካል ማጋራት ስለሚሆን ያለምንም ማንገራገር ከኢስላም ይወጣል። መጸጸት ቢፈልግ እንኳ ወደ ኢስላም ሲገባ የሚባለውን ሸሃደተይን (ሁለቱን ምስክሮች ተናግሮ) አድርጎ ነው የሚሰልመው። ላንተም ይህን ጥያቄህን አንብቦ በከንቱ ላመነህም እንዲሆን ጠቅላላ እውቀት ነው የነገርኩህ። በል መፍትሔውን ክርስቲያኖቹ ይንገሩህ¡
May 29, 2024