ለ ሙስሊሞች ጥያቄ የመጀመርያ ሙስሊም ማነው አዳም ሙሴ ወይስ ሙሃመድ 2 ጥያቄ ነብዩ ሙሃመድ ነው ምትሉት የተናገረውን ትንቢትም በዛው ብትነግሩን..
May 18, 2024ታዲያ አንጻራዊነት ከምን አኳያ? ካልን የቁርአን ትእዛዝ ተቀብሎ የታዘዘ ከኡማው መጀመሪያው እሳቸው ናቸው፦ 6:14 «እኔ *መጀመሪያ ትእዛዝን* ከተቀበለ ሰው ልኾን *ታዘዝኩ*፡፡ ከአጋሪዎችም ፈጽሞ አትኹን ተብያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّىٓ أُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ أَوَّلَ مَنْ أَسْلَمَ ۖ وَلَا تَكُونَنَّ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ “ትእዛዝን ከተቀበለ” የሚለው ይሰመርበት፣ ይህም ትእዛዝ በእሳቸው ላይ የተወረደው ቁርአን ነው፦ 65:5 ይህ *”የአላህ ትእዛዝ ነው”*። ወደ *እናንተም* አወረደው፤ ذَٰلِكَ أَمْرُ ٱللَّهِ أَنزَلَهُۥٓ إِلَيْكُمْ 42:15 በላቸውም፦ ከመጽሐፍ አላህ ባወረደው ሁሉ አመንኩ፤ በመካከላችሁም ላስተካክል *”ታዘዝኩ”*፤ وَقُلْ ءَامَنتُ بِمَآ أَنزَلَ ٱللَّهُ مِن كِتَٰبٍۢ ۖ وَأُمِرْتُ لِأَعْدِلَ بَيْنَكُمُ ከሐዲ የሙስሊም ተቃራኒ ሆኖ አገልግሏል፣ የሙስሊም መጀመሪያ በኣንጻራዊነት ደረጃ እንደተጠቀመ ሁሉ የከሐዲ መጀመሪያ በኣንጻራዊነት ደረጃ ተቀምጧል፦ 68:35 *ሙስሊሞቹን እንደ ከሐዲዎች* እናደርጋለን? 2:41 ከእናንተ ጋር ያለውን መጽሐፍ የሚያረጋግጥ ሆኖ ባወረድኩትም ቁርኣን እመኑ፡፡ በእርሱም *”የመጀመሪያ ከሓዲ”* አትሁኑ፡፡ وَءَامِنُوا۟ بِمَآ أَنزَلْتُ مُصَدِّقًۭا لِّمَا مَعَكُمْ وَلَا تَكُونُوٓا۟ أَوَّلَ كَافِرٍۭ بِهِۦ በእርሱ የመጀመሪያ ከሓዲ አትሁኑ የሚለው ይሰመርበት፣ በቁርአን ማመን የመጀመሪያው ታዛዥ ነቢያችን”ﷺ” እንደሆኑ ሁሉ በቁርአን የመጀመሪያው ከሓዲ እነርሱ ናቸው፤ እኔ የሞባይል የመጀመሪያው ተጠቃሚ ነኝ ብል፤ መጀመሪያነት ከምን አንጻር? ከቤተሰብ? ከከተማ? ከአገር ወይስ ከዓለም? ይህ ቅድሚያ መጠየቅ አለበት፤ ስለ መጀመሪያነት ብዙ ናሙናዎችን መጥቀስ ይቻላል፤ ሙሳ፦ የምእምናን መጀመሪያ ነኝ ብሏል፤ ያ ማለት የሙሳ መጀመሪያነት በአንጻራዊነት ደረጃ እንጂ ከእርሱ በፊት አማኝ አልነበረም ማለት አይደለም፤ የፈርኦን ደጋሚዎች፦ የምእምናን መጀመሪያ ነን ብለዋል፤ ያ ማለት የፈርኦን ደጋሚዎች መጀመሪያነት በአንጻራዊነት ደረጃ እንጂ ከእነርሱ በፊት አማኝ አልነበረም ማለት አይደለም፦ 7፥143 «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም *የምእምናን መጀመሪያ* ነኝ» አለ፡፡ قَالَ سُبْحَٰنَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا۠ أَوَّلُ ٱلْمُؤْمِنِينَ 26፥51 «እኛ *የምእምናን መጀመሪያ* በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡» إِنَّا نَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَٰيَٰنَآ أَن كُنَّآ أَوَّلَ ٱلْمُؤْمِنِينَ ይህንን በቀላሉ ለመረዳት ከባይብል አንድ ናሙና ላቅርብላችሁ። መላእክእት፣ አዳም እና እስራኤል የእግዚአብሔር ልጆች ተብለዋል፦ ኢዮብ 38፥7 አጥቢያ ኮከቦች በአንድነት ሲዘምሩ፥ *የእግዚአብሔርም ልጆች* ሁሉ እልል ሲሉ፥ ሉቃስ 3፥38 የሴት ልጅ፥ የአዳም ልጅ፥ *የእግዚአብሔር ልጅ*። ዘጸአት 4፥22 ፈርዖንንም፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ *”እስራኤል የበኵር ልጄ ነው”*፤ እስራኤል የመጀመሪያ ልጄ ከሆነ ከእስኤል በፊት አዳም እና መላእክት እንዴት ልጆች ተባሉ? “በኵር” ተብሎ የተቀመጠው የግሪኩ ቃል “ፕሮቶ-ቶኮስ” πρωτότοκος ሲሆን ከላይ ለእስራኤል ከዚያ ለኤፍሬም፣ ቀጥሎ ለዳዊት፣ ለጥቆ ለኢየሱስ አገልግሎት ላይ ውሏል፦ ኤርምያስ 31፥9 እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ *”ኤፍሬምም በኵሬ ነውና”*። መዝሙር 89፥27 *እኔም ደግሞ በኵሬ አደርሀዋለው* ከምድር ነገሥታትም ከፍ ይላል። ዕብራውያን 1፥6 *”እግዚአብሔር የበኵር ልጁን ልኮ ወደ ዓለም”* ሲያገባ፦ የእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ ይስገዱለት፥ ይላል። (1980 አዲስ ትርጉም) የበኵር ማለትም የመጀመሪያ ልጅ ማን ነው? እስራኤል ወይስ ኤፍሬም ወይስ ዳዊት ወይስ ኢየሱስ? መልሱ "በኵር" የሚለው ቃል አንጻራዊ ነው ከተባለ እንግዲያውስ "አወል" የሚለየውም ቃል አንጻራዊ እንጂ ፍጹማዊ አይደለም። መልሱ ኢንሻላህ ይቀጥላል.... ✍ከወንድም ወሒድ ዑመር https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
May 18, 2024