ሰላም ቤተሰቦቼ ለምንድን ነው ግን የቶማስ ወንጌል እንደሌሎቹ ወንጌላት መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያልተካተተው?
May 15, 2024ምክንያቱም በቶማስ ያልተጻፈ የ2ኛ ክፍለ ዘመን forgery ስለሆነ ነው። የቶማስ ወንጌል በጊዜው በነበረው Gnosticism አስተሳሰብ የቀረበ እና ስለ ኢየሱስ እናት ማርያምም ስለ ኢየሱስም ከሌሎቹ የ1st Century ወንጌላት ወጣ ያለ አስተምህሮ ያለው መጽሐፍ ነው። በመጀመርያ እና ሁከተኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ የቤ/ያን አባቶችም መጽሐፉ አዲስ እና የGnosticism ትምህርት አዘል መጽሐፍ መሆኑን ስላወቁ በቶማስ እንዳልተጻፈ በየራሳቸው ጽሁፍ ጽፈው አስፍረዋል። ነገር ግን ያ መጽሐፍ canonical ባይሆንም በኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ ቤ/ያናት አስተምህሮ (especially Mariology) ላይ ተጽህኖ አሳድሯል። (which is not good BTW.) በተጨማሪም አንዳንድ ታሪኮች በእስልምናም የገቡ አሉ። መጽሐፉ ውስጥ ካሉ አንዳንድ ታሪኮች መሃል ለመጥቀስ ያህል: • ማርያም የሀና እና Joachim (ኢዮአቄም I think) ልጅ ናት ይላል፤ የሉቃስ ወንጌል ግን የማርያም አባት ኤሊ (Eli) እንደሆነ ነው የሚናገረው። • ኢየሱስ በልጅነቱ ውሃ ሊቀዳ ሲሄድ በልብሱ ቀድቶ ነው የሚያመጣው (ተዓምራዊ በሆነ መንገድ) • ኢየሱስ በልጅነቱ at least ሁለት ህጻናትን ገድሎ አስነስቷል • ማርያም ኢየሱስን ስትወልድ 12 ዓመቷ ነበር ወዘተ ከእውነት ወጣ ያሉ እና gnostic የሆኑ ታሪኮች አለበት። እና earliest church መጽሐፉ በቶማስ ያልተጻፈ አዲስ የፈጠራ ታሪክ መሆኑን ስላወቁ አውግዘውታል።
May 15, 2024