እባካካችሁ የሆነ ነገር በሉም ምን መሰላችሁ avaitor የሚባል virtual ጌም መጫወት ከጀመርኩ አንድ ወር አለፈኝ በዚህ ጊዜ ውስጥ 10 ሺ ብር ተበልቻለሁ እና ውጭ ከሚኖር ጓደኛዬ እንደምንም ብዬ ብር እንዲልክልኝ አደረግሁ የላከልኝን ብር በሰከንድ ውስጥ አስረከብኩ ምን ልሁን ከቁጥጥር ውጭ ሆንኩ አሁን ላይ ዳቦ መግዣ ብር እንኳን የለኝም ጉዳና መውጣቴ ነው ። ብሄድ ይሻለኛል እባካችሁ ምክራችሁን እሻለሁ ምስቅልቅል ያለ ህይወት ልጀምር። ነው አሁን ላይ ያለኝ ስሜት ብታዩት ሂድ ሂድ ነው ሚለኝ😢😢😢😢😢
May 14, 2024ምን ብለን እንድንመክርኽ ነው ያሰብከው ? ይልቅ ውጪ የሚኖረው ጓደኛኽ ሳይልክልኽ ዳቦ እየበላኽ በቆየኽበት መንገድ አርፈኽ ዳቦኽን መብላት ቀጥል ! በተረፈ ይኽን መልዕክት የጻፍክበትን ስልክ እና የለበስከውን ልብስ ኹሉ ባገኘኸው ዋጋ ሸጠኽ ጨዋታኽን ቀጥል ርቃንኽን ገረባ ፍለጋ ስትንከራተት ሕይወት ራሷ በመከራ ዐዲስ ምክር ስለምትመክርኽ ያኔ እኛንም ትመክረናለኽ ! ብሄድ ይሻለኛል ያልከው የት ለመሄድ ነው ? መሄጃ ካለኽ ጥሩ ነው ! ! ለመሞት ከኾነ ከወዲኹ ነፍስኽን ይማረው ራስኽን አጥፍተኽ በመሄድኽ ወለል ብሎ የተከፈተልኽ የገነት ደጃፍ የለም ! እዚኽ የተጫወትከው ጨዋታ በሲዖል ይጫወትብኻል። እዚኽ ተጫዋች ነኽ እዛ መጫወቻ ነኽ ።
May 15, 2024