This question is for all Orthodox, catholic and protestant Christans give me your ideas briefly and explain why you said that from Holy bible only 🙏 ሰማያዊ አማላጅ ማነው? ማርያም፣ ቅዱሳን፣ መላዕክት፣ ኢየሱስ፣ አራቱም፣ ሶስቱ ወይስ ሁለቱ? Be blessed 🙌
May 11, 2024ስለ ምልጃ ስናወራ more ስለ ስላሴ እናወራለን........ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጃችን,አስታራቂያችን,ሊቀ ካህናችን ነው! ይህን ስንል ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ያነሰ ቦታ አለው ማለታችን ሳይሆን እኩልነታቸውን ይገልጻል ሊቀ ካህን(አቅራቢ) ለመሆን የሚያስፈልገው 1. ሰው መሆን አለበት ዕብ 5÷1 2 .የሚራራ መሆን አለበት ዕብ 5÷2(ካህን ኤሊ ግን ለሀና አይራራላትም ነበር) 3 .በእግዚአብሔር የተመረጠ መሆን አለበት (አሮንን እግዚአብሔር አብ እንደመረጠው ኢየሱስ ክርስቶስንም እራሱ እግዚአብሔር አብ ነው የመረጠው መዝ 2, መዝ 110) 4. ሊቀ ካህንነት ለዘላለም የማይቋረጥ መሆን አለበት:: (ዕብራውያን 7 ²³ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ ²⁴ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ²⁵ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል)......(ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ያለ መቆየቱ ምክኒያት ክህነቱ በሰማይ እንዲቀጥል ነው ) ይሄን ሁሉ መሆን ሚችለው ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው:: የኢየሱስ ክርስቶስ የደም መስዕዋት እግዚአብሔር ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ረክቶበታል!☺️ ለዛ ነው ከዛ ደም በኃላ ምናፈሰው ደም ያላስፈለገን! ⭕️እግዚአብሔር አብ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ደም የረካበት ምክኒያት :- 1. ሀጢያት የሌለበት ንፁህ ደም ነው 2.ለእራሱ ለኢየሱስ ክርስቶስ የቀረበ ደም ሳይሆን ስለ እኛ የቀረበ ደም ነው ( በብሉይ ኪዳን ጊዜ ካህናቶች መጀመሪያ ስለ ራሳቸው ሀጢያት መሰዕዋት ያቀርባሉ ከዛ ስለ እስራኤል ሀጢያት መስዕዋት ያቀርባሉ (ዘፅ 27 እና 28 for more info) ) 3. የእራሱ የእግዚአብሔር ደም ነው 4.ደሙ ወደ እግዚአብሔር ይስባል ኤፌ 1÷7 ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ ሊቀ ካህናችን ስለሆነ:- ☑️ በእኛ እና በአብ መካከለኛ የሆነው ኢየሱስ ብቻ ነው! ፩“አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 2፥5 ፪ “ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ፥ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው።” — ዕብራውያን 9፥15 ፫ “ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” — ዮሐንስ 14፥6 ☑️ ጠበቃችን ነው “ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።” — 1ኛ ዮሐንስ 2፥1... አይገርምም ከአብ ዘንድ ተልኮ ስለ እኛ ጠበቃ ነው ☑️ አማላጃችን ነው ፩ “የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” — ሮሜ 8፥34 ፪ “ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።” — ዕብራውያን 7፥25 ፫“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል፤” — ዮሐንስ 14፥15-16
May 12, 2024