Fetena eseralew wixetem arif new gin fetena siders betam yaschenikegnal yihen chinket endet likenis chilalew😔
May 10, 2024ፈተና የምትሰራና ውጤትህ አሪፍ ከሆነ በሁለት መንገድ ላየው እችላለሁ። 1, ፈተናውን የምትሰራው ኮርጀህ ነው። ውጤትህም አሪፍ የሆነው በኩረጃው ነው። ስለዚህ ሰርቀህ ያመጣኀው ነገር ሁሌም ያስጨንቅሃል። ማለት አንተ ጥሩ ለመስራትና አሪፍ ውጤት ለመያዝ ካለህ ከፍ ያለ ፍላጎት አንጻር መኮረጅህ አላስደሰተህም፤ በዚህም ጭንቀት ውስጥ ገብተሃል። ስለዚህ በራስህ አንብበህ ሰርተህ ጭንቀትህን አስወግድ። 2, ፈተናውን የምትሰራው በራስህ አንብበህ ነው። ውጤትህም ጥሩ የሆነው በራስህ ለፍተህ ሰርተህ ባመጣኀው ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ጭንቀትህ ምኑ ጋ ሊመጣ እንደቻለ መገምገም ይኖርብሃል። የምትጨነቀው ከፈተናው በፊት ነው ወይስ በኋላ? ከፈተና በፊት ከሆነ: ከፈተና በፊት የምትመገበውን ምግብ ለይተህ እወቅ። ለፈተና ከመቀመጥህ በፊት በቂ ፈሳሽ ውሃ መውሰድህን አረጋግጥ። (በውሃ እጥረት ምክንያት ሰውነትህ የኦክሲጅን እጥረት ይገጥመዋል። በዚህ ጊዜ በቂ አእምሮህ መጨናነቅ ውስጥ ይገባል። በውሃ እጥረት ምክንያት ሰውነትህ ውስጥ ያሉ መርዛማ ኬሚካሎች መወገድ ስለማይችሉ ይህም ራሱን የቻለ አለመመቸትና ጭንቀት ያመጣል። ይህን ጭንቀት ደግሞ በውሃ አስወግድ።) በቂ እንቅልፍ መተኛትህን አረጋግጥ። ሆን ብሎ ሊያጨናንቅህ ከሚመጣ ጓደኛ ራቅ። "እኔ አንብቤያለሁ። እደፍነዋለሁ።...) እያለ ራስህን እንድትጠራጠር ከሚያደርግ ጓደኛ ራቅ። ከፈተናው በኋላ ከሆነ: ፈተናው እንዳለቀና ከዚያ በኋላ የፈተናህ ውጤት በፈጣሪ እጅ (ባነበብከው ልክ እንደምታገኝ) እንደሆነ ማመን መቻል አለብህ። ፈተናህን ጨርሰህ እንደወጣህ ስለዚያ ፈተና ከማንም ጋር በምንም መልኩ ማውራት የለብህም። ትክክል ስለሆነው ስህተት ስለሆነው ከጓዶችህ ጋር በፍጹም አታውራ። ከንቱ ጸጸት፣ ጭንቀትና ንዴት እንጂ ሌላ አታተርፍም። ሆን ብለው "እኔ ሰርቼዋለሁ። ደፍኜዋለሁ።..." ከሚሉ ሰዎችም ራስህን አግልል። በፍጥነት ከፈተና ጣቢያው መራቅን ልምድህ አድርግ። እኔ በተማሪነት ዘመኖቼ ይህን ካወቅኩት በኋላ በመተግበሬ በጣም የተሳካ ጊዜ አሳልፌያለሁ። የምትጨናነቅበት ምክንያት ከፈተናው ጋር በተያያዘ ነው ወይስ በሌላ የህይወትህ ጉዳይ? ይህንንም ዘርዘር አድርገህ አጢነው። በተረፈ ፈጣሪ እንዳለ ለሚያምን ሰው ጭንቀት በፈጣሪ እንደመካድ ነው የሚቆጠረው። ምክንያቱም ፈጣሪ እንዳለ ለሚያምን ሰው ፈጣሪ ለሁሉ ነገሩ የወሰነለት ነገር እንዳለ እና የተወሰነለትን እንደሚያገኝ፣ ያልተወሰነለት እንደማይገጥመው ስለሚረዳ ጭንቀትን ያስወግዳል። አይዞህ! መልካም ጁምዐ ማታ መልካም ቅዳሜ ሌሊት
May 10, 2024