ሰላም ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ለመስራት አስቤያለሁ እና እዛ ስራ ፈልጌ እስከማገኝ ደግሞ ለትንሽ ግዜም የሚያቆየኝ(የሚያስጠጋኝ) ቤተሰብም ይሁን የማውቀው ሰው የለኝም😥 ስለዚህ ቤት ተከራይቼ ነው ስራ ለመፈለግ ያሰብኩት እና በትንሹ ለቤት ኪራይ ለታክሲ እና ለምግብ ወጪ ለ 4 ወር የሚሆን ግዜ ስንት ብር ያስፈልገኛል ? እንዳታልፉት ወገኖቼ መልስ ስጡኝ
May 08, 2024ዝቅተኛ ቤት ኪራይ >ከ3000-3500 ×4= 12000-14000 >ትራንስፖርት ስራ ለመፈለግ ብዙ ቦታ ከሄድክ ግማሽ መንገድ ባስ + ግማሹን ታክሲ = ባስ ደርሶ መልስ 20 + ታክሲ ደርሶመልስ 30 =50 በሣምንት አራት ቀን ከወጣህ 50×4= 200 ወደ ወር 200×4=800 ወደ አራት ወር 800×4= 3200 ከፍ አርገህ 4000 በለው >ምግብ እንደ አጠቃቀምህ ነው ውጪ ከተጠቀምቅ ምሣና እራት ብታ 240 ብር ሊወስድብህ ይችላል። በትንሹ ስናየው 240×90=21,600 ራስህ ካበሰልክ ልትቀንስ ትችላለህ ወጪውን ግን እንደ አጠቃቀምህም በጣም ሊጨምርብህ ይችላል 21,600+4000+14000= 39,600 አካባቢ ሊፈጅብህ ይችላል። ከዛም ሊበልጥ ይችላል ወጪው። ብቻ እግዚአብሔር ቶሎ ስራ እንድታገኝ ይርዳህ።
May 08, 2024