ትውውቃችን ሁለታችንንም በምታውቀን ልጅ ነው:: እቃ ላቀብልላት አጊንቼው በጣም እረጋ ያለ ተግባቢ ሰው ስለነበር በ1ቀን ለብዙ ሰዓት ስለብዙ ነገር ነበር ያወራነው :: ከዛን ልጅቷ እንደተመቸውት እንደነገራት ነገረችኝ: እሷም አውሪው አሪፍ ልጅ ነው ሰው አክባሪ ሐይማኖተኛ ነው አለችኝ:: እሄ የሆነው የዛሬ አመት አከባቢ ነው: በስልክ አንዳንዴ በደንብ እናወራለን በአካል ድጋሚ 2ቀን ተገናኘን እሱንም በአጋጣሚ:: እኔ ፍቅር ምናምን ምል ሰው አይደለሁም ቤተክርስቲያን እቤትና ስራ ሂወቴ እንዲ ነው :: መምህር ነኝ በቅርቡ ለስራ ከከተማ ወጥቻለሁ ስሄድም እያወራን ስላልነበር እልነገርኩትም ግን አሁን በደንብ ነው ምናወራው እሱም በተመሳሳይ ስራ ሊመጣም እንደሆነ ነገረኝ :: ግን እኔን ያሳሰበኝ ፩ ያለሱ ምንም አለማሰቤ ይገርመኛል ፪ ላግኝሽ ሲለኝ እንዴትም ማግኘት ነበረብኝ / እኔ ስችል ላግኝክ ማለት አብሬው ጊዜ ማሳለፍ ልጁን በደንብ ማወቅ ነበረብኝ እያልኩ እራሴን እወቅሳለሁ! ፫ አንዳንዴ በሰላም እንደ ፍቅር ያወራኛል አንዳንዴ አያወራኝም ዮነ እንደ ኩራት ያደርገዋል ደና አዎ ይሆናል መልሱ:: እኔ ደግሞ ወድጄዋለሁ ጥያቄ. አሁን ስለሱ ማሰብ እንዴት ልተው ? ስለኔ ያለውን ስሜትስ እንዴት ልወቅ ? ሲመጣስ እንዴት አውርቼው መቅረብ ማየትና እችላለሁ ??
May 07, 2024በደንብ አላወራ በሚልሽ ጊዜ አንቺ space ስጪው (ለትንሽ ጊዜ እራሱ እስኪያወራሽ/እስኪደውልልሽ ተብቂው) ነግሮች ከሱ እንዲመጡ ጊዜ ስጪው ከዛ ስላንቺ ያለውን ስሜት ቀስ በቀስ ትረጅያለሽ
May 08, 2024