selam sewoch orthodoxawyan eski ye diakon besufkad "tensake "ymilewn mexmur kalachu lakulgn
May 07, 2024አዲስ የትንሳኤ መዝሙር በ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው ✞ ትንሣኤከ ለእለ አመነ ትንሳኤከ ለእለ አመነ ብርሃነከ ከፈኑ ዲቤነ /2/ የትንሳኤው በጎል የሰው ልጆች ሂወት ኢየሱስ ክርስቶስ ተነስቷል በእውነት በዝግ መቃብር ውስጥ ተነሳ ሳይከፍተው አዳምንም ከሞት ከሲኦል አወጣው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/ አዝ__ የሲኦል መውጊያዋ ፍላፅው ተነስቷል የኛ መድኃኔዓለም ሞትን ድል አድርጓል የእዳ ደብዳቤ በሲኦል ያለውን ደምስሶት ተነሳ አውጥቶ ነብሳቱን በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/ አዝ__ ማርያም መቅደላዊት የጠራሽ በስምሽ በዓይንሽ ያየሽውን ሐዋርያት ይስሙሽ መላዕክቱም አሉ ተነስቷል ተነስቷል የነገራችሁን እዩተሰ ተፈፅሟል በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/ አዝ__ የሞት ሐይሉ ታየ ሲዋረድ በጌታ በድንግል ማርያም ልጅ በፍጥረት አሌንታ እናቱ እናቴ እመቤቴ ወልዳው በትንሳኤው ደሞ ሰላሜን አገኘው በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/ አዝ__ ለትንሳኤው ልጆች ለምናምን ለኛ ብርሐንን ላከልን ላይጨልም ዳግመኛ እንዘምር ለክብሩ ከበሮ ይመታ ተነስቷል ኢየሱስ እንዳይቆም እልልታ በትንሳኤው ተነስተን ዘመርን የምህረቱን አመታት መቁጠር ጀመርን/2/ ዘማሪ በሱፍቃድ አንዳርጋቸው 🔎 በ21 መዝሙር ለመቀላቀል 👇 ➯@m_ezmur21 ➯@m_ezmur21 🔔✅ሼር