ጥያቄ ለክርስቲያን ወገኖች በእብራውናን 5፥7 መሰረት እውን እየሱስ ተሰቅሏልን? እውን ወዶና ፈቅዶ ከተሰቀለ ብርቱ ምልጃ ጩኸትና ለቅሶው አስፈላጊ ነው? “እርሱም በስጋው ወራት #ከሞት ሊያድነው ወደሚችል ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፥ እግዚአብሔርንም ስለ መፍራቱ #ተሰማለት፤” — ዕብራውያን 5፥7 በቅንነት መልሱልኝ
May 04, 2024እሺ በዚው ምራፍ ከላይ ባሉት ቁጥሮች ሊቀ ካህናት ሰው መሆናቸውን ተናግሮአል። ኢየሱስም እንዲሁ በሊቀ ካህንነት ለማገልገል ሰው መሆን አለበት። በዚህ ቁጥር ላይ ፥ እንደሰውነቱ አንዱን የኢየሱስን ሕይወት ገጽታ ያቀርባል ። የሚደርስብንን ፈተናና ድካማችንን ጨምሮ ኢየሱስም እንደኛ ሰው ነበር። ምንም እንኳ የራሱ የእግዚአብሔር ልጅ ቢሆንም፥ እንደ እኛው ሁሉ ማንኛውንም መከራ ተቀብሎአል። ድንጋዩን ወደ እንጀራ መለወጥና ሲርበው መመገብ ይችል ነበር! እርሱ ግን ያንን አላደረገም .(ማቴ. 4፥2-4)፡፡ በተያዘበት ጊዜም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የመላእክት ሰራዊት ደርሰው እንዲታደጉት ማድረግ ይችል ነበር፤ እርሱ ግን ያንን አላደረገም (ማቴ. 26፥53)፡፡ ተራ ሰዎች መከራና ስቃይን እንደሚቀበሉ ሁሉ፥ እርሱም መከራና ስቃይን ተቀበለ። እርሱ ራሱ የተለያየ ችግርን ተቀብሎአልና፥ ኢየሱስ በማንኛውም ሁኔታችን ሊራራልን ይችላል (ዕብ. 2:181 4:15) የኢየሱስ መከራ ከእኛ መከራ ይልቅ እጅግ የከፋ ነበር። እዚ ጋር ስለ ኢየሱስ ሲናገር በትህትና በመታዘዙም እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው ይላል። በመስቀል ላይ ከመሞት እንዲድን ኢየሱስ ጸልዮ ነበር (ማር 14:35-36) እግዚአብሔር ግን ያን ጸሎት አልተቀበለውም። እርግጥ ነው እግዚእብሔር ከሞት ሊያድነው ይችል ነበር፤ እንደዚያ ግን አላደረገም። ይሁን እንጂ፥ ከሦስት ቀን በኋላ ከሞት በማስነሳት እግዚአብሔር የኢየሱስን ጸሎት መልሶለታል፡፡ የአለምን ሃጢያት በሙሉ ኢየሱስ ተሸክሞ ስለኛ ሲሞት የእግዚአብሔርን ቁጣ አበረደ።
May 04, 2024