Selam , yenat yabat fkr alawkm bebzu fetena adeku beyesew bet eyezorku adeku lij eyalehu yederesubgn negeroch trauma honew yrebshugnal ahun 23 amet honognal sewu tnsh tekotito kanageregn hula behayle qal nw mimelsew erasen protect yadereku Ymeslegnal. Bchegna negn bchayen yekerehu Ymeslegnal eskahun yakoyegn amlak yawkal nege godana liwudeq weym yeteshale bota alawqm gn btm bchegninet ysemagnal. Alawkm Hulem endih ysemagnal keftegna yehone chnket alebgn ena degmo yemrsat chgr bzu negerochn resalehu. Mn hogne yhon edt Ende hulum sw aynet normal life menor echilalehu.
May 03, 2024ምን በጣም እንደገረመኝ ታዉቂያለ? እኔ እናት እና አባቴ ቤት ነዉ ያደኩት። አባታችን በጣም ደብዳቢ ሰካራም ነበር። እናታችን በጣም ድሀ ስለነበርን ትንንሽ ስራዎች ለመስራት ታናናሽ ልጆቹን እና የቤት ማስተዳደሩን ቢያንስ 8አመት ሲሞላኝ ጣለችብኝ። እንደ ሮቦት እንጂ ፍቅር እንደሚያስፈልገዉ ልጅ አታየኝም። ለሌሎቿ ልጆች እንስፍስፍ ናት ለኔ ግን ልቧ ድንግጥም አይልም። የእናትም አባትም ፍቅር ሳላይ ስላደኩ ነገሮችን ለብቻዬ ነበር የማደርጋቸዉ። ብዙ ቦታ በስራ ምክንያት ታፍኜ እራሱ ቤተሰብ ጋር ደዉይ ስሉኝ ግደሉኝ ቤተሰብ የለኝም ነዉ ያልኩት። ማንንም አላምንም። ወንድ ጠላቴ ነዉ። የመርሳት ችግር ሁሌ ነዉ ምክንያቱም ዉስጤ ድብልቅልቅ ይልብኛል። የምወስናቸዉ ዉሳኔዎች ትክክል ካልሆኑ ለብቻዬ መቀመቅ ስለምወርድ አይምሮዬን አስጨንቀዋለዉ። የትራዉማዉ ህመም ሙሉ ሰዉነቴን አድክሞታል። የሚገርመዉ ግን ከዉጪ ስታይ የደላኝ የሀብታም ልጅ ነዉ የምመስለዉ። ሰዉ ትንሽ ተናገረኝ ማለት ህይወቴን ሊያጠፋዉ ነዉ የሚመስለኝ ቶሎ እቆጣለዉ። እራሴን ለመከላከል ወዲያዉ እርምጃ እወስዳለሁ። በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ እራሱ አባቴ አናት የሚበጠብጥ ስድብ ሰድቦኝ 2 ትንንሽ ሻንጣዎች ይዤ ከቤት ወጥቼ ባዶ ወና ቤት ተከራይቼ እራሴን እያስታመምኩ ነዉ። እኔ 32 አመቴ ድረስ አይምሮዬ ጥቅም አልባ ሆኖ ነዉ የኖርኩት በነሱ ምክንያት። አንቺ ገና ልጅ ነሽ። ሳይኮሎጂስቶች አናግረሽ ቶሎ ዳኚ። እንዴት እንደሚጎዳ ስለማዉቅ ነዉ እንዲህ የምልሽ።
May 04, 2024