For christian ppl yzin poem mels efalgalw ba sreat anbibiuna ba chewanat asredu! ለእየሱስ ባሪያዎች! ~ የመሲህ ባሮች ሆይ - አንድ ጥያቄ አለን የተረዳው ካለ - መልሱን እንሻለን ጌታ ግፍ አቅቶት - ሰዎች ከገደሉት አለቀ አከተመ - የታል አምላክነት?! ሰዎች የሰሩትን - በሱ ላይ ሲያደርሱ ጌታ ግብራቸውን - ፈቅዶ ነው በራሱ? እንዲያ ከሆነማ - ምንኛ ታደሉ?! ፍቅሩን ይቸራሉ - ፈቃዱን ሲሞሉ። ባደረሱት ሁሉ - አልፎ ከተከፋ እንግዲህ ምን ይባል? ሀይሉ ከኮሰሰ - ሀይላቸው ከሰፋ?! ግን እንጠይቃለን - ለመልስ አትንፈጉ ማለባበስ ይቅር - ይመለስ በወጉ ፈጣሪዋን አጥታ - ዐለም ስትዋትት ሰው ወደ ማን ነበር - የሚያስበው ፀሎት? ፍጡር ፈጣሪውን - ካፈር ሲያደባየው ሰባቱን ሰማያት - ማነበር ያቆየው? ምስማር ተቸንክሮ - ሲያሸልብ ፈጣሪ ዓለም ቀርታ ነበር - ያለ አስተናባሪ? የሰማይ መላእክት - ምንኛ ለገሙ?! እጁ ተቸንክሮ - ዋይታውን ሲሰሙ? እንጨቱም ታምር ነው - አቅሙ መቋቋሙ አምላክ ያክል ነገር - ችሎ መሸከሙ ስለቱስ ጭቃኔው - ብረቱ ምስማሩ አካሉን ሰንጥቆ - ስቃይ ማሳደሩ ጉድ በሉ እሄን ጌታ - በአይሁድ የሚረታ ማጅራቱን ታንቆ - ታስሮ የሚመታ ኋላስ ራሱ ነቃ - ከሞት አንሰራራ ወይስ ጌታ አገኘ - ህይወት የሚዘራ?!
May 03, 2024Hahahaaaaaa መልሱን ከፈለከው ልብህ እውነት ሽታ፤ በትዕግስት ሁነህ አድምጠኝ ለአንድ አፍታ፤ ምን መታደል ብቻ ፤ ይህንን ለመግለፅ ቃል የለውም አቻ፤ ጌታ ኢየሱስ ሲሞት፤ በዓለም ማን ነግሶበት፤ ነው አይደል ጥያቄው ፤ እውነት በጣም ነው ሚደንቀው፤ ግና ሞት ራሱ ምንድነው?፤ አሟሟቱስ ቢሆን እንደምን ያለነው፤ ስማኝ ፥ መለኮት አይሞትም፤ ግን ደግሞም አልሞተም ፤ በምድር ሲመላለስ ከሰማይ ሳይጎድል፤ አድኖን ተዛምዶን አቁሞናል በድል፤ ያሳዝናል በጣም፤ አንተ የላከው ግጥም ፤ እንኳን ለሃይማኖቴ ለእምነትህ አይጥም፣ ምክንያቱም ፣ ነፍስ እንዳትበሰብስ ዘለአለም እንድትኖር ፣ ሰብካችሁ አልነበር፤ ታዲያ አሁን እንዴት ፤ ስጋችን እንጂ ነፍሳችን ላትሞት ፣ ተፈጥራለች ለህይወት፣ ይቅርታ ጊዜ ስላነሰኝ ግጥሙን ተውኩት ነገር ግን ሞት ምን እንደሆነ እወቅ እናም ጌታችን ትስብእቱ(ሰውነቱ) ነው እንጂ መለኮቱ (አምላክነቱ) አልሞተም አይሞትምም ስገረፍ ሲሰቃይ የነበረውም መለኮት አይደለም የአዳም ስጋ እንጂ በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ ለእንጨቱ(ሎቱ ስብሃት ለመስቀሉ) ለችንካሩ ለሚገርፉትም ጭምር ኃይላቸውና የሚያበረታቸው እሱ ነበር ነገር ግን አንተ አዕምሮህ ከፈጠረው የፈጣሪ ባህሪ ውጣ ምክንያቱም ያንተ አዕምሮ የአንተን ባህር እንኳን በስርዓት አያውቅም ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ነው ወይስ አይደለም ? ከሆነ ይሄ ጥያቄ መና ነው ደግሞም የሰማይ መላእክት እርሱን የሚጠብቁት መከላከያ ወይም ፖሊስ አይደሉም እርሱ አነርሱን ይጠብቃቸዋል እንጂ በመጨረሻም የተነሳው ሲሞት ምን እንደተባለ ከሰማህ ይገባሃል '' ነፍሱን ከስጋው ለየ'' በኃላ ደግሞ ነፍሱን ከስጋው አዋሃደ 🤷 ማን? የለየው ። ጌታ ሆይ ከሰው አዕምሮ በላይ መሆንክን ሳስብ ማሰቤን ማቆም እፈልጋለሁ ነገር ግን አንተን ማሰብ ያስደስታል እና ማቆም አልችልም ተመስገን🙏🙏🙏 እኔም ጥያቄ ልጠይቅህ ?
May 03, 2024