ሰላም ሰዎች am 20 F የሲጋራ ሱሰኛ ነኝ 2 አመት ምናምን። ከዚ ሱስ ቶሎ መውጣት እፈልጋለሁ ግን መውጣት የሚቻል የሚቻል አይመስለኝም እየከበደኝ ነው። ደሞ የሚገርመው ማንም ሱሰኛ መሆኔን አያውቅም ማወቅ አይደለም በፍፁም ሱሰኛ ናት ተብዬ የምገመት ሰው አይደለሁም። ከእኔና ከፈጣሪ ውጪ ማንም አያውቅም። እና ደሞ የ1ኛ አመት ተማሪ ነኝ F ደርድሬአለሁ በዚሁ ምክንያት ብዙ ጊዜ class እቀራለሁ ምናምን, ብቻ ሁሉም ነገር እየከበደኝ ነው የትምህርቴንም ነገር ማስተካከል አለብኝ እና ምን ልላችሁ ነው.. ምናልባት ከዚ በፊት ሱስ ውስጥ ገብታችሁ የወጣችሁ ሰዎች እባካችሁ ተባበሩኝ የወጣችሁበትን መንገድ ምናምን ልምዳችሁን ንገሩኝ ተስፋ ስጡኝ እባካችሁ..የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ነኝ...
Apr 26, 2024ከሲጋራ በላይ የነበረ ሱስ ውስጥ ነበርኩ ፣ ሁሌም ካረኩት በኋላ እጸጸት ነበር ፣ ከፈጣሪ እርቅ ነበር ። እረጅም አመት ወጣትነቴን በልቶኝ ነበር። 7 አመት ሙሉ ተዋጋሁት ። ከዚህ ወዲያ አላረገውም ብዬ ቤተክርስቲያን ሄጄ የማልኩበት ቀን ቢቆጠር 50 ጊዜ ይሆናል። ከሰው ተደብቄ ነበር እማረገው ፣ ከዛ እራሴን እንዴት እንደሞጎዳኝ አወኩኝ ። መልካሙ ነገር በተግባሩ እሚሰማሽ ጸጸት ነው ። አሁን እምጸልየው ነገር ቢኖር ጸጸቴን አትውሰድብኝ ብዬ ነው ። በቅድሚያ በዚህ ነገር ያጣሺውን ነገር ሁሉ ጻፊው ፣ አፍ ያሸታል ፣ ከሰው መሃል ያዋርዳል ፣ ሱስ ሆኖ ይገዛሻል ፣ እንደፈለገ ያዝሻል ፣ እንደደሰት አረገዋለው ትዩ ይሆናል እምታዢውም ይመስልሻል ግን እሱ ነው እሚያዝሽ ፣ ሱስ አለቃሽ ይሆናል ፣ ንጉስሽ ይሆናል ። ባጨስሽ ቁጥር እሱን አስቢ ፣ ቤተክርስቲያን ሂጂ ተንበርክከሽ አልቅሺ ፈጣሪ እንዲረዳሽ ከልብሽ ጠይቂው ። 50 ጊዜ አቆማለው ብለሽ ማይ 50 ጊዜ ቃልሽን ስበሬ ፣ በያንዳንዱ ቃልሽን በሰበርሽ ጊዜ እራስሽን እና አምላክሽን ሳይሆን ሱስሽን በራስሽ ስላነገስሽ ይቅርታ ጠይቂ ። ቃልሽን እየሰበርሽ ጸጸቱ ሲጨምር 100 ኛው ጊዜ ላይም ቢሆን እስከመጨረሻው ታቆሚያለሽ ። እኔ ይህን ነበር ያረኩት ፣ ስህተት እና ሃጥያት እንድሆነ እያወኩ ብዙ ምክንያት ደርድሬ አረገዋለው ፣ ጸጸቱ እና ምህላው ደግሜ ባረኩት ቁጥር እየጨመረ መጣ ፣ የሆነ ቀን ተጠየፍኩት ፣ አሁን ነጻ ከወጣው 3 አመት ሞላኝ ህይወቴ ተለውጧል ። ትልቁ ጦርነት እራስን ማሸነፍ ነው ፣ ፈጣሪ እረድቶኝ አሳክቼዋለው ፣ አንቺም በርቺ ፣ ተሰናከይ ፣ ተጸጸቺ አምላክሽን ይቅርታ ጠይኪ ፣ እየወደቅሽ ነጻ ትወጫለሽ ። ከሱስ ለመውጣት ትልቁ መፍቴ አለመግባት ነው ፣ ስለዚህ ሌላ ሱስ ውስጥ ላለመግባት በጣም ተጠንቀቂ
Apr 27, 2024