Endet nachihu guys. 21 amete new neger gin betam kechaha negn(around 56kilos). Ena ahun bulk lemadreg ena gym lemegemer eyasebku new. Eski Arif protein shake yemibal nigerugn ena sint wer yufegal at least 65 kg gar lemedres. thank you 😊.
Apr 21, 2024Look bulking has nothing to do with protein or supplements: ’በተፈጥሮ ቀጭን ሁነህ ጂም እየሰራህም ቀጮ ሁነህ ቀርተህ ከበዛ እዚህ ግባ ማይባል ትንሽዬ ቅርጽ ይዘህ ለ1-2 ዓመት ከቆየህ ወይም ደግሞ መጀመሪያ ዓመት ሁለት አመት ሰውነትህ ጨምሮ አሁን ግን አልጨምር ካለህ እየሰራህ ያለው ስህተት በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። እሱም አለመብላት ነው። ይህ ቀላል ይመስላል ግን፣ ምግብ በሁለት አይነት መንገድ ትሳሳታለህ። አንዱ በቀን ሚገባህን ፕሮቲን ከምግብህ አለማግኘትህ ነው። በኪሎህ 1 ግራም ብለናል፣ ስለዚህ 60 ኪሎ ቀጮ ከሆንክ 60 ግራም በቀላሉ ከምግብህ ማግኘት ትችላለህ። ስለምግብ ፖስት ያደረግነውን ወደላይ ሂደህ አንብብ። ግን ቀጥሎ ምትሳሳተው፣ ካሎሪ ሰርፕለስ ላይ አለመሆንህ ነው። አልጨምር አልኩኝ ሚል ሰው ካሎሪ ሰርፕለስ ላይ አይደለም፣ ያን ያህል ቀላል ነው። ካሎሪ ሰርፕለስ ማለት ሰውነትህ ለቀን ተቀን እንቅስቃሴው (ስፖርትንህም ጨምሮ) ከሚያስፈልገው ሃይል በላይ መብላት አለብህ ማለት ነው። ከ 300 እስከ 500 ካሎሪ ትርፍ ላይ መሆን አለብህ። ያለበለዚያ መጀመሪያ አካባቢ ነው እንጂ ከዛ በኋላ ሰውነትህ አልጨምር ያላል። በቀን 300 ካሎሪ ሰርፕለስ ላይ ከሆንክ ካልኩሌት ስታደርገው በወር 1 ኪሎ ሰውነትህ ላይ ጭማሪ ይመጣል ማለት ነው። ካሎሪ ሰርፕለስ ላይ መሆን bulk ይባላል። bulk ቢያንስ ቢያንስ ለ መጀመሪያው 1 አመትህ አድርገህ ሰውነትህ በደንብ ጨምሮ ምትደስበት ሳይዝ ስትደርስ ወይም በስህተት ከሚገባው በላይ ጮማ ከጨመርክ ብቻ cut አድርግ። cut ማለት ደግሞ በቀን ከሚያስፈልግህ 500 ካሎሪ አሳንሰህ መመገብ ሲሆን ሰውነትህ የግድ ካስቀመጠው የስብ ክምችት አንድዶ የተቀረውን ሃይል ያመነጫል ማለት ነው። ሰውነት ምትቀንሰው እንደዛ ነው፣ ሎሚ ያለው ሙቅ ውሃ፣ ምናምን ቀበቶ፣ አቮካዶ ምናምን እያልክ አመታት ብትቆይ በቀን ከምታነደው በታች ካልተመገብክ በምንም ተዓምር ስብ አይቀንስም። ስለዚህ አሁንም እንደግመዋለን። በተፈጥሮ hard gainer ከሆንክ እና ኪሎ ለመጨመር ሚከብድህ ከሆነ በየቀኑ ምትመገበው ላይ 500 ካሎሪ ጨምረህ ኪሎህን ከ 1 ሳምንት በኋላ እይ። አሁንም አልጨምር ካለ እሱ ላይ 100 ካሎሪ ጨምርና ከንደገና እይ። ልክ ኪሎህ መጨመር ሲጀምር በልክ ምታደርግበት ምግብ ብዛት አገኘህ ማለት ነው። ነገር ግን ይህ ብዛት ሚያስጨምርህ ለ 2-3 ኪሎ ቢሆን ነው፣ ከንደገና አልጨምር ማለቱ አይቀርም። የዛኔ ምን ታደርጋለህ? ቀላል ነው፣ ከንደገና ምትመገበውን ብዛት ትጨምራለህ ማለት ነው። ችግሩ በተፈጥሮ hard gainer ከሆንክ እስከ 4000 ካሎሪ ድረስ ራሱ መመገብ ግዴታ ሊሆንብህ ይችላል ማለት ነው። ስለዚህ ሌላ አማራጭ ስለሌለህ የግድ በየቀኑ መመገብ አለብህ ማለት ነው። በየቀኑ ምብላት ካልቻልክ አትጨምርም፣ ለዚህም ነው ከክብደቱ ምግቡ ይከብዳል ሲባል ምትሰማው። ምክንያቱም ከሆነ ግዜ በኋላ ምትመገበው ብዛት በጣም ብዙ ይሆናል። በቀን እስከ 5-6 ግዜ ሊደርስ ራሱ ይችላል። ለዚህም ነው ካሎሪ በጣም የበዛበት ምግብ፣ ልክ እንደ ለውዝ ቅቤ እና የመሳሰሉት እነሱን ከወተት ወይ ከበሶ ቀላቅለህ በ አንድ ሰርቪንግ እስከ 1000 ካሎሪ ሚደርስ ሼክ ሰርተህ በ ደቂቃዎች ውስጥ መጠጣት ትችላለህ።’ The following “👆” was not my writing but i think it will help u to understand about bulking and how exactly it works.
Apr 23, 2024