Selam አንድ ፍልስፍና"philosophy" ፍልስፍና ለመባል ምን ምን ሞሞላት አለበት!! plzz don't scroll it Amesegnalehu
Apr 18, 2024በመጀመርያ የሀሳቡ አዲስነት ከዚ ቀደም ከሚወሩም ሆነ ከሚነሱ አስተሳሰቦች መለየት አለበት አለዚያ እንደ በቀቀን የፊቱን ወሬ መድገም ይሆናል! ሁለተኛ የጥያቄው ተገቢነት ፍልስፍና በአብዛኛው ከመታዘብ እና ከመጠየቅ ይጠነሰሳልና ጥንስሱ ያማረ መሆን አለበት!ትዝብትህን ወይም ምልከታህን በትክክለኛ ጥያቄ ማጀብ አለብህ! ሶስተኛ ምክንያታዊነት(አመክንዮ or logic) ምልከታህ ጥያቄህ እና አስተሳሰብህ በተገቢው የምክንያታዊነት መስመር ካልተጓዘ በስሜት የተረታ ይሆናል ስለዚህ ለእያንዳንዱ ነጠሊ አሳብ ጥሩ ምክንያት ላይ መንተራስ ግድ ይሏል። ያው በመጨረሻ ወይም በመጀመርያ ራሱ ፈላስፋው መኖር አለበት!
Apr 19, 2024